እግዚአብሔር ከፊታቸው አሳድዶ ያስወጣቸው አሕዛብ እንዳደረጉትም ሁሉ፣ በየኰረብታው ላይ ዕጣን አጤሱ፤ እግዚአብሔርንም የሚያስቈጣ ክፉ ነገር አደረጉ።
ዘዳግም 18:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ፣ በዚያ የሚኖሩት አሕዛብ የሚፈጽሙትን አስጸያፊ መንገድ አትከተል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አምላክህ ጌታ ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ፥ በዚያ የሚኖሩት አሕዛብ የሚፈጽሙትን አስጸያፊ መንገድ አትከተል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ በዚያ የሚኖሩ ሕዝቦች የሚፈጽሙትን አጸያፊ ልማድ ሁሉ አትከተል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ ጊዜ እነዚያ አሕዛብ የሚያደርጉትን ርኵሰት ታደርግ ዘንድ አትማር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ ጊዜ እነዚያ አሕዛብ የሚያደርጉትን ርኩሰት ታደርግ ዘንድ አትማር። |
እግዚአብሔር ከፊታቸው አሳድዶ ያስወጣቸው አሕዛብ እንዳደረጉትም ሁሉ፣ በየኰረብታው ላይ ዕጣን አጤሱ፤ እግዚአብሔርንም የሚያስቈጣ ክፉ ነገር አደረጉ።
እግዚአብሔር ከእስራኤላውያን ፊት ያስወገዳቸውን የአሕዛብን ርኩሰት ተከትሎ፣ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ዐጠነ፤ ወንዶች ልጆቹንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ።
ከዚህም ላይ የካህናቱና የሕዝቡ መሪዎች ሁሉ፣ አስጸያፊ የሆኑትን የአሕዛብን ልማዶች በመከተልና በኢየሩሳሌም የተቀደሰውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በማርከስ፣ ባለመታመናቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሱ ሄዱ።
ትእዛዜን ጠብቁ፤ ከእናንተ በፊት በምድሪቱ የኖሩ ሰዎች ካደረጓቸው አስጸያፊ ድርጊቶች አንዱንም አትፈጽሙ፤ በእነዚህም ራሳችሁን አታርክሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።’ ”
አለዚያ አማልክታቸውን በሚያመልኩበት ጊዜ የሚፈጽሟቸውን አስጸያፊ ተግባራት ሁሉ ታደርግ ዘንድ ያስተምሩሃል፤ በአምላክህ በእግዚአብሔርም ላይ ኀጢአት ትሠራለህ።
አምላክህ እግዚአብሔር እነርሱን ከፊትህ ካስወጣቸው በኋላ በልብህ፣ “ይህችን ምድር እንድወርስ እግዚአብሔር ወደዚህ ያመጣኝ፣ ከጽድቄ የተነሣ ነው” አትበል። በዚህ አይደለም፤ እነዚህን አሕዛብ እግዚአብሔር ከፊትህ የሚያሳድዳቸው በክፋታቸው ምክንያት ነው።
ምድራቸውን ገብተህ የምትወርሳት ከጽድቅህ ወይም ከልብህ ቅንነት የተነሣ ሳይሆን፣ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ የማለላቸውን ቃል ለመፈጸም አምላክህ እግዚአብሔር እነዚህን አሕዛብ ከክፋታቸው የተነሣ ከፊትህ ስለሚያባርራቸው ነው።