La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 18:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከቤተ ሰቡ ንብረት ሽያጭ ላይ ገንዘብ ቢቀበል እንኳ፣ ባልንጀሮቹ ከሚያገኙት ጥቅም እኩል ይካፈላል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከቤተሰቡ ንብረት ሽያጭ ላይ ገንዘብ ቢቀበል እንኳን ባልንጀሮቹ ከሚያገኙት ጥቅም እኩል ይካፈላል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከቤተሰብ ንብረት ሽያጭ ገንዘብ የሚቀበል ቢሆንም እንኳ እርሱም ሌሎቹ ካህናት በሚያገኙት መጠን ድርሻውን ይቀበላል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከአ​ባ​ቶቹ ከብት ዋጋ ሌላ እንደ ባል​ን​ጀ​ሮቹ ከመ​ብል ድር​ሻ​ውን ይወ​ስ​ዳል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከተሸጠው ከአባቶቹ ከብት ዋጋ ሌላ እንደ ባልንጀሮቹ ከመብል ድርሻውን ይወስዳል።

Ver Capítulo



ዘዳግም 18:8
11 Referencias Cruzadas  

ካህናቱና ሌዋውያኑም ሙሉ ጊዜያቸውን ለእግዚአብሔር ሕግ አገልግሎት ማዋል ይችሉ ዘንድ፣ በኢየሩሳሌም የሚኖረው ሕዝብ ተገቢውን ድርሻ እንዲሰጣቸው አዘዘ።


በዚያ ቀን ስጦታው፣ በኵራቱና ዐሥራቱ የሚቀመጥበትን ዕቃ ቤት የሚጠብቁ ሰዎች ተሾሙ። እነርሱም በየከተሞች ዙሪያ ከሚገኙት የዕርሻ ቦታዎች ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት የካህናቱንና የሌዋውያኑን ድርሻ ወደ ዕቃ ቤቱ ማምጣት ነበረባቸው፤ ይሁዳ በሚያገለግሉ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ተሠኝተው ነበርና።


በዘሩባቤልና በነህምያም ዘመን እስራኤል ሁሉ ለመዘምራኑና ለበር ጠባቂዎቹ የየዕለቱን ድርሻ ይሰጡ ነበር፤ የሌሎቹን ሌዋውያን ድርሻም ለብቻ ያስቀምጡ ነበር፤ ሌዋውያኑም ለአሮን ዘሮች ድርሻቸውን ያስቀምጡላቸው ነበር።


“ ‘ከዕርሻ ምርትም ሆነ ከዛፍ ፍሬ፣ ማንኛውም ከምድሪቱ የሚገኝ ዐሥራት የእግዚአብሔር ነው፤ ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ነው።


ከእያንዳንዱም ዐይነት አንዳንድ አንሥቶ ለእግዚአብሔር የተለየ ቍርባን በማድረግ ያቅርብ፤ ይህም የኅብረት መሥዋዕቱን ደም ለሚረጨው ካህን ይሰጥ።


“በመገናኛው ድንኳን በሚያገለግሉበት ጊዜ ለሚሠሩት ሥራ ደመወዝ እንዲሆናቸው ከእስራኤል የሚወጣውን ዐሥራት ሁሉ ለሌዋውያን ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ።


ያቀረቡላችሁን ሁሉ እየበላችሁና እየጠጣችሁ በዚያ ቤት ተቀመጡ፤ ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል። ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው ቤት አትዘዋወሩ።


በእግዚአብሔር ፊት ቆመው እንደሚያገለግሉት ሌዋውያን ወንድሞቹ፣ እርሱም በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ያገልግል።