ዘዳግም 18:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሌዋዊ ከሚኖርበት ከየትኛውም በእስራኤል ካሉት ከተሞችህ መካከል በፍጹም ፈቃድ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ስፍራ ቢመጣ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በእስራኤል ካሉት ከተሞችህ መካከል፥ አንድ ሌዋዊ ከሚኖርበት ከየትኛውም በፍጹም ፈቃድ ጌታ ወደ መረጠው ስፍራ ቢመጣ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሌዋዊ ከሚኖርበት ከማንኛውም የእስራኤል ከተማ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ቦታ ለመምጣት ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖረው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንድ ሌዋዊ ሰው ከሚቀመጥባቸው በእስራኤል ሁሉ ዘንድ ካሉት ከተሞች ከአንዲቱ፥ በፍጹም ልብም ሊያገለግል እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ቢመጣ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ሌዋዊ ሰው ከሚቀመጥባቸው በእስራኤል ሁሉ ዘንድ ካሉት ከአገር ደጆች ከአንዲቱ ቢወጣ፥ በፍጹም ፈቃድም እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ቢመጣ፥ |
እግዚአብሔርን አንዲት ነገር እለምነዋለሁ፤ እርሷንም እሻለሁ፤ ይኸውም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ውበት አይ ዘንድ፣ በመቅደሱም ሆኜ አሰላስል ዘንድ ነው።
በሌላ ስፍራ ሺሕ ቀን ከመኖር፣ በአደባባይህ አንዲት ቀን መዋል ይሻላል፤ በክፉዎች ድንኳን ከመቀመጥ ይልቅ፣ በአምላኬ ቤት ደጅ መቆም እመርጣለሁ።
ከዚያም ከተማውን መካከል በማድረግ ወደ ምሥራቅ ሁለት ሺሕ ክንድ፣ ወደ ደቡብ ሁለት ሺሕ ክንድ፣ ወደ ምዕራብ ሁለት ሺሕ ክንድ፣ ወደ ሰሜን ሁለት ሺሕ ክንድ ከከተማው ውጭ ለካ፤ እነዚህንም ቦታዎች ለከተሞቹ የግጦሽ መሬት ያደርጓቸዋል።
ከዚያም አምላካችሁ እግዚአብሔር ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ፣ እኔ የማዝዛችሁን ሁሉ፦ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁንና ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፣ ዐሥራቶቻችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፣ እንዲሁም ለእግዚአብሔር የተሳላችኋቸውን ምርጥ ነገሮች ሁሉ ወደዚያ ታመጣላችሁ።
እግዚአብሔር ለስሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ በሚመርጠው ስፍራ ከበግና ከፍየል ወይም ከመንጋህ አንዱን እንስሳ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ፋሲካ አድርገህ ሠዋው።
በእናንተ ኀላፊነት ሥር ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ የምትጠብቁትም ከእግዚአብሔር እንደሚጠበቅባችሁ በግድ ሳይሆን በፈቃደኝነት፣ ለጥቅም በመስገብገብ ሳይሆን ለማገልገል ባላችሁ ጽኑ ፍላጎት ይሁን፤