ዘዳግም 18:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኮሬብ ጉባኤ በተደረገበት ዕለት፣ “እንዳልሞት የአምላክህ የእግዚአብሔርን ድምፅ አልስማ፤ እንዲህ ያለውንም አስፈሪ እሳት ደግሜ አልይ” ብለህ አምላክህን እግዚአብሔርን የጠየቅኸው ይህን ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኮሬብ ጉባኤ በተደረገበት ዕለት፥ ‘እንዳልሞት የጌታ የእግዚአብሔርን ድምፅ አልስማ፤ እንዲህ ያለውንም አስፈሪ እሳት ደግሜ አልይ’ ብለህ አምላክህን ጌታን የጠየቅኸው ይህን ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በሲና ተራራ ላይ በተሰበሰባችሁበት ቀን እሞታለሁ ብለህ በመፍራት እግዚአብሔር ዳግመኛ እንዳይናገርህና የመገለጡን ሁኔታ የሚያመለክተውን አስፈሪ እሳት እንዳታይ ጠይቀህ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችሁን እግዚአብሔርን በኮሬብ በተሰበሰባችሁበት ቀን፦ ‘እንዳንሞት የአምላካችን የእግዚአብሔርን ድምፅ ደግሞ አንስማ፤ ይህችን ታላቅ እሳት ደግሞ አንይ’ ብላችሁ እንደ ለመናችሁት ሁሉ። |
እግዚአብሔር በስብሰባው ቀን፣ በእሳት ውስጥ ሆኖ ለእናንተ የተናገራቸውንና ቀድሞ ጽፏቸው የነበሩትን ዐሥሩን ትእዛዞች በእነዚህ ጽላት ላይ ጻፋቸው። እግዚአብሔርም እነርሱን ለእኔ ሰጠኝ።
በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን ሁለት የድንጋይ ጽላት እግዚአብሔር ሰጠኝ፤ በተሰበሰባችሁበት ዕለት እግዚአብሔር ከተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ለእናንተ የነገራችሁ ትእዛዞች ሁሉ በእነርሱ ላይ ነበሩባቸው።