La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 14:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን ከሚያመሰኩት ወይም ሰኰናቸው ከተሰነጠቀ እንስሳት መካከል ግመልን፣ ጥንቸልንና ሽኮኮን አትብሉ፤ እነርሱ ቢያመሰኩ እንኳ፣ ሰኰናቸው የተሰነጠቀ ባለመሆኑ፣ በሥርዐቱ መሠረት በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን ከሚያመሰኩት ወይም ሰኰናቸው ከተሰነጠቀ እንስሳት መካከል ግመልን፥ ጥንቸልንና ሽኮኮን አትብሉ፤ ምክንያቱም እነርሱ ቢያመሰኩሁም፥ ሰኰናቸው አልተሰነጠቀምና እነዚህ ለእናንተ ርኩሶች ናቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን ሰኮናቸው ያልተከፈለውንና የማያመሰኩትን እንስሶች አትብሉ፤ በዚህም ዐይነት ግመል፥ ጥንቸልና ሽኮኮ የመሳሰሉትን አትብሉ፤ እንደነዚህ ያሉት እንስሶች የሚያመሰኩ ቢሆኑም ሰኮናቸው ያልተከፈለ በመሆኑ የረከሱ ሆነው ይቈጠራሉ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን ከሚ​ያ​መ​ሰኩ ወይም ሰኰ​ና​ቸው ከተ​ሰ​ነ​ጠቀ እነ​ዚ​ህን አት​በ​ሉም፤ ግመ​ልን፥ ሽኮ​ኮን፥ ጥን​ቸ​ልን አት​በ​ሉም፤ ያመ​ሰ​ኳ​ሉና፥ ነገር ግን ሰኰ​ና​ቸው አል​ተ​ሰ​ነ​ጠ​ቀ​ምና እነ​ዚህ ለእ​ና​ንተ ርኩ​ሳን ናቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን ከሚያመሰኩ ወይም ሰኮናቸው ከተሰነጠቀ እነዚህን አትበሉም፤ ግመልን፥ ጥንቸልን፥ ሽኮኮን አትበሉም። ያመሰኳሉና፥ ነገር ግን ሰኮናቸው አልተሰነጠቀምና እነዚህ ለእናንተ ርኩሶች ናቸው።

Ver Capítulo



ዘዳግም 14:7
10 Referencias Cruzadas  

ሰኰናው የተሰነጠቀውን የሚያመሰኳውን ማንኛውንም እንስሳ መብላት ትችላላችሁ።


ሽኮኮ ያመሰኳል፤ ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ ግን በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን።


ጥንቸል ያመሰኳል፤ ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ ግን በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን።


ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የማያውለው ግን ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራን ሞኝ ሰው ይመስላል።


ሰኰናው ስንጥቅ የሆነውን፣ ለሁለት የተከፈለውንና የሚያመሰኳውን ማንኛውንም እንስሳ ብላ።


ዐሣማም እንደዚሁ ርኩስ ነው፤ ምንም እንኳ ሰኰናው የተሰነጠቀ ቢሆንም፣ ስለማያመሰኳ፣ እርሱ ለእናንተ ንጹሕ አይደለም፤ የእነዚህን ሥጋ አትብሉ፤ ጥንባቸውንም አትንኩ።


ሃይማኖታዊ መልክ አላቸው፤ ኀይሉን ግን ክደዋል። ከእነዚህ ራቅ።


እግዚአብሔርን እናውቃለን ይላሉ፤ ዳሩ ግን በተግባራቸው ይክዱታል፤ አስጸያፊዎች፣ የማይታዘዙና ለበጎ ሥራ የማይበቁ ናቸው።