ይህ የደረሰባቸውም የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ያዘዘውን የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ከመስማት ይልቅ ኪዳኑን ስላፈረሱ ነበር፤ ትእዛዞቹን አላደመጡም፤ ደግሞም አልፈጸሙም።
ዳንኤል 9:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ ኀጢአት ሠርተናል፤ በድለናልም፤ ክፋትን አድርገናል፤ ዐምፀናልም፤ ከትእዛዝህና ከሕግህ ዘወር ብለናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኛ ግን ክፉዎችና ዐመፀኞች ሆነን ኃጢአት በመሥራት በድለናል፤ ሕግህንና ትእዛዞችህን ከመፈጸም ቸል ብለናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃጢአትን ሠርተናል፥ በድለንማል፥ ክፋትንም አድርገናል፥ ዐምፀንማል፥ ከትእዛዝህና ከፍርድህም ፈቀቅ ብለናል፥ |
ይህ የደረሰባቸውም የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ያዘዘውን የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ከመስማት ይልቅ ኪዳኑን ስላፈረሱ ነበር፤ ትእዛዞቹን አላደመጡም፤ ደግሞም አልፈጸሙም።
ይህን የማደርገውም የቀድሞ አባቶቻቸው ከግብጽ ምድር ከወጡበት ጊዜ አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ በፊቴ ክፉ ድርጊት ስለ ፈጸሙና ለቍጣ ስላነሣሡኝ ነው።’ ”
እንዲህ ስል ጸለይሁ፤ “አምላኬ ሆይ፤ ኀጢአታችን ከራሳችን በላይ ሆኗል፤ በደላችንም እስከ ሰማያት ደርሷል፤ አምላኬ ሆይ፤ ፊቴን ወደ አንተ ቀና ለማድረግ ፈራሁ፤ እጅግም ፈራሁ።
በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀናል፤ ሐሰት ተናግረናል፤ አምላካችንን ከመከተል ዘወር ብለናል፤ ዐመፃንና ግፍን አውርተናል፤ ልባችን የፀነሰውን ውሸት ተናግረናል።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከአንተ መኰብለል አብዝተናል፤ በአንተም ላይ ዐምፀናል፤ ኀጢአታችን ቢመሰክርብንም እንኳ፣ ስለ ስምህ ብለህ አንድ ነገር አድርግልን።
እንግዲህ ዕፍረታችንን ተከናንበን እንተኛ፤ ውርደታችንም ይሸፍነን፤ እኛም አባቶቻችንም፣ እግዚአብሔር አምላካችንን በድለናልና፤ ከልጅነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ አምላካችንን እግዚአብሔርን አልታዘዝንም።”
ወዳጆችህ ሁሉ ረስተውሃል፤ ስለ አንተም ግድ የላቸውም። ጠላት እንደሚመታ መታሁህ፤ እንደ ጨካኝም ቀጣሁህ፤ በደልህ ታላቅ፣ ኀጢአትህም ብዙ ነውና።
ይህም የሆነው ስላደረጉት ክፋት ነው። እነርሱም ሆኑ እናንተ ወይም አባቶቻችሁ ላላወቋቸው ለሌሎች አማልክት በማጠንና በማምለክ አስቈጥተውኛል።
“እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ እኔ ግን በትእዛዙ ላይ ዐመፅ አድርጌ ነበር፤ እናንተ ሕዝቦች ሁሉ ስሙ፤ መከራዬንም ተመልከቱ፤ ወይዛዝርቶቼና ጐበዛዝቴ፣ ተማርከው ሄደዋል።
“አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዴት ተጨንቄአለሁ! በውስጤ ተሠቃይቼአለሁ፤ በልቤ ታውኬአለሁ፤ እጅግ ዐመፀኛ ሆኛለሁና፤ በውጭ ሰይፍ ይፈጃል፤ በቤትም ውስጥ ሞት አለ።
እነዚህ ከሰይፍ የተረፉት፣ ከእኔ ዘወር ባለ አመንዝራ ልባቸውና ጣዖትን በተከተለ አመንዝራ ዐይናቸው የቱን ያህል እንዳሳዘኑኝ፤ በአሕዛብ ምድር ሆነው ያስታውሱኛል፤ ካደረጉት ክፋትና ከፈጸሙት ርኩስ ተግባር ሁሉ የተነሣም ራሳቸውን ይጸየፋሉ።
መላው እስራኤል አንተን ባለመታዘዝ ሕግህን ተላልፏል፤ ዘወርም ብሏል። “በአንተ ላይ ኀጢአትን ስለ ሠራን፣ በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴ ሕግ የተጻፈው መሐላና ርግማን ፈሰሰብን።
“አሁንም ሕዝብህን ከግብጽ ምድር በብርቱ እጅ ያወጣህ፣ እስከዚህም ቀን ድረስ ስምህ እንዲታወቅ ያደረግህ፣ ጌታ አምላካችን ሆይ፤ እኛ ኀጢአትን ሠርተናል፤ አንተንም በድለናል።
እግዚአብሔር በሆሴዕ መናገር በጀመረ ጊዜ፣ እግዚአብሔር “ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ተለይታ ታላቅ ምንዝርና እያደረገች ስለ ሆነ፣ ሄደህ አመንዝራ ሴት አግባ፤ የምንዝርና ልጆችንም ለራስህ ውሰድ” አለው።
ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከትእዛዞቼ ፈቀቅ ብላችኋል፤ አልጠበቃችኋቸውምም፤ ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “እናንተ ግን፣ ‘የምንመለሰው እንዴት ነው?’ ትላላችሁ።