ዳንኤል 7:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከዚህ በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ በፊቴም የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ በጣም ኀይለኛ የሆነ አራተኛ አውሬ ነበር፤ ትልልቅ የብረት ጥርሶች ነበሩት፤ ያደቅቅና ይበላ፣ የቀረውንም ሁሉ በእግሮቹ ይረጋግጥ ነበር። ከርሱ በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየ ሲሆን፣ ዐሥር ቀንዶች ነበሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚያ በኋላ አራተኛውን አውሬ አየሁ፤ እርሱም አስፈሪ፥ አስደንጋጭና በጣም ኀይለኛ ነበር፤ ይህም አውሬ የሚቦጫጭቅባቸውና የሚሰባብርባቸው ታላላቅ የብረት ጥርሶች ነበሩት። የተረፈውንም በእግሮቹ ይረግጠው ነበር፤ ካለፉትም አውሬዎች ሁሉ የተለየ ሆኖ ዐሥር ቀንዶች ነበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፥ እነሆም፥ የምታስፈራና የምታስደነግጥ እጅግም የበረታች፥ ታላላቅም የብረት ጥርሶች የነበሩአት አራተኛ አውሬ ነበረች፥ ትበላና ታደቅቅ ነበር፥ የቀረውንም በእግርዋ ትረግጥ ነበር፥ ከእርስዋም በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየች ነበረች፥ አሥር ቀንዶችም ነበሩአት። |
በራእይ እግዚአብሔር ወደ እስራኤል ምድር አመጣኝ፤ ከፍ ባለ ተራራ ላይ አኖረኝ፤ ከተራራውም በስተ ደቡብ፣ ከተማ የሚመስሉ ሕንጻዎች ነበሩ።
ከዚያም ሌላ ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆ፤ ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶች የነበሩት፣ በራሶቹም ላይ ሰባት አክሊል የደፋ ታላቅ ቀይ ዘንዶ ታየ።
ዘንዶውም በባሕሩ ዳር ቆሞ ነበር። ከዚያም አንድ አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ እርሱም ዐሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፤ በቀንዶቹም ላይ ዐሥር ዘውዶች፣ በራሶቹም ላይ የስድብ ስሞች ነበሩት።
“ያየሃቸው ዐሥሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ፣ ዐሥር ነገሥታት ናቸው፤ ነገር ግን ከአውሬው ጋራ ለአንድ ሰዓት እንዲነግሡ ሥልጣን ይቀበላሉ።
ከዚያም መልአኩ እንዲህ አለኝ፤ የምትደነቀው ለምንድን ነው? የሴቲቱን፣ እርሷ የተቀመጠችበትንም፣ እንዲሁም ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶች ያሉትን የአውሬውን ምስጢር እነግርሃለሁ።
ያየኸው አውሬ ቀደም ሲል ነበረ፤ አሁን ግን የለም፤ በኋላም ከጥልቁ ጕድጓድ ይወጣል፤ ወደ ጥፋቱም ይሄዳል። ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘ የምድር ነዋሪዎች አውሬው ቀድሞ የነበረ፣ አሁን ግን የሌለ፣ በኋላም የሚመጣ መሆኑን ሲያዩ ይደነቃሉ።