Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዳንኤል 2:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ለዳንኤልም ምስጢሩ በሌሊት በራእይ ተገለጠለት፤ ዳንኤልም የሰማይን አምላክ አመሰገነ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በዚያኑ ሌሊት ምሥጢሩ ለዳንኤል በራእይ ተገለጠለት፤ ስለዚህ የሰማይን አምላክ እንዲህ ሲል አመሰገነ፦

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የዚያን ጊዜም ምሥጢሩ በሌሊት ራእይ ለዳንኤል ተገለጠለት፥ ዳንኤልም የሰማይን አምላክ አመሰገነ።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 2:19
16 Referencias Cruzadas  

እንዲህ አላቸው፤ “ቃሌን ስሙ፤ “የእግዚአብሔር ነቢይ በመካከላችሁ ቢኖር፣ በራእይ እገለጥለታለሁ፤ በሕልምም እናገረዋለሁ።


በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምስጢሩን ለአገልጋዮቹ ለነቢያት ሳይገልጥ፣ ምንም ነገር አያደርግም።


“ከዚህ በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ በፊቴም የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ በጣም ኀይለኛ የሆነ አራተኛ አውሬ ነበር፤ ትልልቅ የብረት ጥርሶች ነበሩት፤ ያደቅቅና ይበላ፣ የቀረውንም ሁሉ በእግሮቹ ይረጋግጥ ነበር። ከርሱ በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየ ሲሆን፣ ዐሥር ቀንዶች ነበሩት።


እግዚአብሔር ምስጢሩን ከሚፈሩት ወዳጆቹ አይሰውርም፤ ኪዳኑንም ይገልጥላቸዋል።


እግዚአብሔር ለእነዚህ አራት ወጣቶች በማንኛውም ሥነ ጽሑፍና ትምህርት ዕውቀትንና ማስተዋልን ሰጣቸው፤ ዳንኤልም ማንኛውንም ራእይና ሕልም የመረዳት ችሎታ ነበረው።


በሚያስጨንቅ የሌሊት ሕልም ውስጥ፣ ከባድ እንቅልፍም በሰዎች ላይ በወደቀ ጊዜ፣


እኔም እንዲህ አልሁት፤ “የጠቢባን አለቃ ብልጣሶር ሆይ፤ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ ውስጥ እንዳለ ዐውቃለሁ፤ ምንም ዐይነት ምስጢር አያስቸግርህም፤ ያየሁት ሕልም እነሆ፤ ተርጕምልኝ።


የጠለቀውንና የተሰወረውን ነገር ይገልጣል፤ በጨለማ ያለውን ያውቃል፤ ብርሃንም ከርሱ ጋራ ይኖራል።


እስራኤላውያንም ይህን ሲሰሙ ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ከዚያም የሮቤልና የጋድ ወገኖች የሚኖሩበትን አገር በጦርነት ለማጥፋት የመሄድን ነገር አላነሡም።


የዛፉ ጕቶ ከነሥሩ እንዲቀር መታዘዙ፣ ሥልጣን ከሰማይ መሆኑን ስታውቅ መንግሥትህ እንደሚመለስልህ ያመለክታል።


ዳንኤል እንዲህ አለ፤ “አራቱ የሰማይ ነፋሳት ታላቁን ባሕር ሲያናውጡት ሌሊት በራእይ አየሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios