ዳንኤል 11:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰሜኑም ንጉሥ፣ የደቡቡን ንጉሥ ግዛት ይወርራል፤ ነገር ግን አፈግፍጎ ወደ ገዛ አገሩ ይመለሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ የሶርያ ንጉሥ የግብጽን ንጉሥ ግዛት ለመውረር ይመጣል፤ ነገር ግን በመጣበት እግሩ ወደ አገሩ እንዲመለስ ይገደዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም ወደ ደቡብ ንጉሥ መንግሥት ይገባል፥ ነገር ግን ወደ ገዛ ምድሩ ይመለሳል። |
አማልክታቸውን፣ የብረት ምስሎቻቸውን፣ ከብርና ከወርቅ የተሠሩ የከበሩ ዕቃዎቻቸውን ይማርካል፤ ወደ ግብጽም ይወስዳል። ለጥቂት ዓመታትም ከሰሜኑ ንጉሥ ጋራ ከመዋጋት ይቈጠባል።
እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉ ግን ድል ይነሣቸዋል፤ ምክንያቱም እርሱ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ነው፤ ከርሱ ጋራ ያሉ የተጠሩት፣ የተመረጡትና የታመኑትም ዐብረው ድል ይነሣሉ።”