ዳንኤል 11:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አማልክታቸውን፣ የብረት ምስሎቻቸውን፣ ከብርና ከወርቅ የተሠሩ የከበሩ ዕቃዎቻቸውን ይማርካል፤ ወደ ግብጽም ይወስዳል። ለጥቂት ዓመታትም ከሰሜኑ ንጉሥ ጋራ ከመዋጋት ይቈጠባል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአማልክታቸውንም ምስሎች ከወርቅና ከብር ዕቃዎች ጋር ማርኮ ወደ ግብጽ ይወስዳል፤ ለጥቂት ዓመቶችም የግብጹ ንጉሥ የሶርያን ንጉሥ በጦርነት ለማጥቃት አይነሣም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አማልክቶቻቸውንና ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎቻቸውን ከብርና ከወርቅም የተሠሩትን የከበሩትን ዕቃዎች ወደ ግብጽ ይማርካል፥ እስከ ጥቂትም ዓመት ድረስ ከሰሜን ንጉሥ ጋር ሳይዋጋ ይቀመጣል። |
“እኔም በዚያች ሌሊት በግብጽ ምድር ላይ ዐልፋለሁ፤ ከሰውም ከእንስሳም የተወለደውን የበኵር ልጅ ሁሉ እገድላለሁ፤ የግብጽን አማልክት ሁሉ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
የእስራኤል አምላክ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በቴብስ አምላክ በአሞን ላይ፣ በፈርዖን ላይ፣ በግብጽና በአማልክቷ ላይ፣ በነገሥታቷም ላይ፣ እንዲሁም በፈርዖን በሚታመኑት ላይ ቅጣት አመጣለሁ፤
በወንድሞቹ መካከል ቢበለጽግም እንኳ፣ የምሥራቅ ነፋስ ከምድረ በዳ እየነፈሰ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል፤ ምንጩ ይነጥፋል፤ የውሃ ጕድጓዱም ይደርቃል። የከበረው ሀብቱ ሁሉ፣ ከግምጃ ቤቱ ይበዘበዛል።
በዚህ ጊዜ ግብጻውያን እግዚአብሔር ከመካከላቸው የገደለባቸውን በኵሮቻቸውን ይቀብሩ ነበር፤ እግዚአብሔር በግብጽ አማልክት ላይ ፈርዶ ነበርና።
መሠዊያዎቻቸውን አፍርሱ፤ የማምለኪያ ዐምዶቻቸውን ሰባብሩ፤ የአሼራ ምስል ዐምዶቻቸውን በእሳት አቃጥሉ፤ የአማልክታቸውን ጣዖቶች ቈራርጣችሁ ጣሉ፤ ስማቸውንም ከእነዚያ ስፍራዎች ላይ አጥፉ።
እርሱም፣ “እንዴት፣ ‘ምን ሆንህ’ ብላችሁ ትጠይቁኛላችሁ? የሠራኋቸውን አማልክቴንና ካህኔን ወስዳችሁ ሄዳችኋል፤ ምን የቀረኝ ነገር አለ?” አላቸው።