ዳንኤል 11:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ታላቅ ሰራዊት አደራጅቶ ኀይሉንና ብርታቱን በደቡብ ንጉሥ ላይ ያነሣሣል፤ የደቡብ ንጉሥም ቍጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ ኀያል ሰራዊት ይዞ ጦርነትን ያውጃል፤ ነገር ግን ከተዶለተበት ሤራ የተነሣ መቋቋም አይችልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ትልቅ የጦር ኀይል አደራጅቶ በድፍረት በግብጽ ንጉሥ ላይ ይዘምታል፤ የግብጽ ንጉሥም በበኩሉ እጅግ ታላቅ የሆነ የጦር ኀይል አዘጋጅቶ የመጣበትን ጦር ይመክታል፤ ነገር ግን የግብጹ ንጉሥ ሤራ ስለሚደረግበት አይሳካለትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በታላቅም ሠራዊት ሆኖ ኃይሉንና ልቡን በደቡብ ንጉሥ ላይ ያስነሣል፥ የደቡብም ንጉሥ በታላቅና በብዙ ሠራዊት ሆኖ በሰልፍ ይዋጋል፥ ነገር ግን አሳብ በእርሱ ላይ ይፈጥራሉና አይጸናም። |
“አሁንም እውነቱን እነግርሃለሁ፤ እነሆ፤ ሦስት ሌሎች ነገሥታት በፋርስ ይነሣሉ፤ አራተኛውም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ እጅግ ባለጠጋ ይሆናል። በባለጠግነቱም እጅግ በበረታ ጊዜ፣ ሌላውን ሁሉ አሳድሞ በግሪክ መንግሥት ላይ ያስነሣል።
“በመጨረሻው ዘመን የደቡብ ንጉሥ ጦርነት ያውጅበታል፤ የሰሜን ንጉሥም በፈረሰኞችና በሠረገሎች፣ በብዙ መርከቦችም እንደ ማዕበል ይመጣበታል፤ ብዙ አገሮችን ይወርራል፤ እንደ ጐርፍም እየጠራረገ በመካከላቸው ያልፋል።