ዳንኤል 11:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሁንም እውነቱን እነግርሃለሁ፤ እነሆ፤ ሦስት ሌሎች ነገሥታት በፋርስ ይነሣሉ፤ አራተኛውም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ እጅግ ባለጠጋ ይሆናል። በባለጠግነቱም እጅግ በበረታ ጊዜ፣ ሌላውን ሁሉ አሳድሞ በግሪክ መንግሥት ላይ ያስነሣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም አሁን የምነግርህ ነገር እውነት ነው።” ያም ሰው የሚመስለው መልአክ እንዲህ ሲል ንግግሩን ቀጠለ፦ “ሌሎች ሦስት ነገሥታት በፋርስ ላይ ይነግሣሉ፤ ከእነርሱ የሚከተለው አራተኛው ንጉሥ ከሌሎቹ ይልቅ በሀብት የከበረ ይሆናል፥ ከሀብቱም የተነሣ ኀይሉ በበረታ ጊዜ ሌሎቹን መንግሥታት በማስተባበር በግሪክ መንግሥት ላይ ይነሣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም እውነትን አሳይሃለሁ። እነሆ፥ ሦስት ነገሥታት ደግሞ በፋርስ ይነሣሉ፥ አራተኛውም ከሁሉ ይልቅ እጅግ ባለጠጋ ይሆናል፥ በባለጠግነቱም በበረታ ጊዜ በግሪክ መንግሥት ላይ ሁሉን ያስነሣል። |
በፋርስ ንጉሥ በአርጤክስስ ዘመን ቢሽላም፣ ሚትሪዳጡ፣ ጣብኤልና ተባባሪዎቹ ወደ አርጤክስስ ደብዳቤ ጻፉ። ደብዳቤው የተጻፈው በአራማይክ ፊደል፣ በአራማይክ ቋንቋ ነበረ።
የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት፣ ብልጣሶር ለተባለው ዳንኤል ራእይ ታየው። መልእክቱ እውነት ነው፤ ስለ ታላቅ ጦርነትም የሚገልጽ ነበረ። መልእክቱንም ይገነዘብ ዘንድ በራእይ ማስተዋል ተሰጠው።
“ታላቅ ሰራዊት አደራጅቶ ኀይሉንና ብርታቱን በደቡብ ንጉሥ ላይ ያነሣሣል፤ የደቡብ ንጉሥም ቍጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ ኀያል ሰራዊት ይዞ ጦርነትን ያውጃል፤ ነገር ግን ከተዶለተበት ሤራ የተነሣ መቋቋም አይችልም።
“እነሆም፤ ሁለተኛው አውሬ ድብ ይመስል ነበር፤ በአንድ ጐኑ ከፍ ብሏል፤ በአፉ ውስጥ በጥርሶቹ መካከል ሦስት የጐድን ዐጥንቶች ነበሩት። እርሱም፤ ‘ተነሥ፤ እስክትጠግብ ድረስ ሥጋ ብላ!’ ተባለ።
አውራ በጉም ወደ ምዕራብ፣ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ በቀንዱ ሲጐሽም አየሁ። ምንም ዐይነት እንስሳ ሊቋቋመው አልቻለም፤ ከእጁም ሊያድን የሚችል አልነበረም፤ የፈለገውን ሁሉ አደረገ፤ ታላቅም ሆነ።
በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውም፣ “እነሆ፤ እኔ ሁሉን ነገር አዲስ አደርጋለሁ” አለ፤ ደግሞም፣ “ይህ ቃል የታመነና እውነት ስለ ሆነ ጻፍ” አለ።