Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዳንኤል 11:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “ታላቅ ሰራዊት አደራጅቶ ኀይሉንና ብርታቱን በደቡብ ንጉሥ ላይ ያነሣሣል፤ የደቡብ ንጉሥም ቍጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ ኀያል ሰራዊት ይዞ ጦርነትን ያውጃል፤ ነገር ግን ከተዶለተበት ሤራ የተነሣ መቋቋም አይችልም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “ትልቅ የጦር ኀይል አደራጅቶ በድፍረት በግብጽ ንጉሥ ላይ ይዘምታል፤ የግብጽ ንጉሥም በበኩሉ እጅግ ታላቅ የሆነ የጦር ኀይል አዘጋጅቶ የመጣበትን ጦር ይመክታል፤ ነገር ግን የግብጹ ንጉሥ ሤራ ስለሚደረግበት አይሳካለትም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በታላቅም ሠራዊት ሆኖ ኃይሉንና ልቡን በደቡብ ንጉሥ ላይ ያስነሣል፥ የደቡብም ንጉሥ በታላቅና በብዙ ሠራዊት ሆኖ በሰልፍ ይዋጋል፥ ነገር ግን አሳብ በእርሱ ላይ ይፈጥራሉና አይጸናም።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 11:25
6 Referencias Cruzadas  

ግልፍተኛ ሰው ጠብ ያነሣሣል፤ ታጋሽ ሰው ግን ጠብን ያበርዳል።


ሥሥታም ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን ይባረካል።


ወንዶች ልጆቹም ለጦርነት ይዘጋጃሉ፤ እስከ ጠላት ምሽግ ደርሶ የሚዋጋና ሊቋቋሙት እንደማይቻል ጐርፍ የሚጠራርግ ታላቅ ሰራዊት ያሰባስባሉ።


“አሁንም እውነቱን እነግርሃለሁ፤ እነሆ፤ ሦስት ሌሎች ነገሥታት በፋርስ ይነሣሉ፤ አራተኛውም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ እጅግ ባለጠጋ ይሆናል። በባለጠግነቱም እጅግ በበረታ ጊዜ፣ ሌላውን ሁሉ አሳድሞ በግሪክ መንግሥት ላይ ያስነሣል።


“በመጨረሻው ዘመን የደቡብ ንጉሥ ጦርነት ያውጅበታል፤ የሰሜን ንጉሥም በፈረሰኞችና በሠረገሎች፣ በብዙ መርከቦችም እንደ ማዕበል ይመጣበታል፤ ብዙ አገሮችን ይወርራል፤ እንደ ጐርፍም እየጠራረገ በመካከላቸው ያልፋል።


“የደቡቡ ንጉሥ ይበረታል፤ ነገር ግን ከጦር አዛዦቹ አንዱ ከርሱ የበለጠ የበረታ ይሆናል፤ ግዛቱም ታላቅ ይሆናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos