አሞጽ 7:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እግዚአብሔር ይህንም አሳየኝ፤ ጌታ እግዚአብሔር በእሳት ሊፈርድ ተዘጋጀ፤ እሳቱም ታላቁን ጥልቅ አደረቀ፤ ምድሪቱንም በላ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ አሳየኝ፤ እነሆም፥ ጌታ እግዚአብሔር በእሳት ለመፍረድ ጠራ፤ እርሷም ታላቁን ቀላይና ምድርን በላች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ እግዚአብሔር የገለጠልኝ ሌላውም ራእይ ይህ ነው፤ እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር የእሳት ቅጣት ፍርድ አስተላለፈ፤ እሳቱም ባሕሩን በልቶ ካደረቀው በኋላ ምድርን ማቃጠል ጀመረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ አሳየኝ፤ እነሆም ጌታ እግዚአብሔር ለመፍረድ በቃሉ እሳትን ጠራ፤ እርስዋም ታላቁን ቀላይና ምድርን በላች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ አሳየኝ፥ እነሆም፥ ጌታ እግዚአብሔር በእሳት ለመፍረድ ጠራ፥ እርስዋም ታላቁን ቀላይና ምድርን በላች። |
የዳዊት ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ካደረጋችሁት ክፋት የተነሣ፣ ቍጣዬ እንዳይቀጣጠል፣ ማንም ሊያጠፋው እስከማይችል እንዳይነድድ፣ በየማለዳው ፍትሕን አድርጉ፤ የተበዘበዘውን ሰው፣ ከጨቋኙ እጅ አድኑት።
እናንተ የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች፤ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፤ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ፤ አለዚያ ስለ ሠራችሁት ክፋት፣ ቍጣዬ እንደ እሳት ይንበለበላል፤ ሊገታውም የሚችል የለም።
እንዲህም በል፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ እኔ በአንቺ ላይ ተነሥቻለሁ፤ ሰይፌን ከሰገባው እመዝዛለሁ፤ ጻድቁንም፣ ክፉውንም ከአንተ ዘንድ አስወግዳለሁ።
“ሰዶምንና ገሞራን እንደ ገለበጥኋቸው፣ አንዳንዶቻችሁን ገለበጥሁ፤ ከእሳት እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤” ይላል እግዚአብሔር።
ጌታ እግዚአብሔር ይህን አሳየኝ፤ የንጉሡ የመኸር እህል ከተሰበሰበ በኋላ ገቦው መብቀል በጀመረ ጊዜ፣ እርሱ የአንበጣ መንጋ እንዲፈለፈል አደረገ።
ከዚህ በኋላ እነሆ፤ በሰማይ የተከፈተ በር አየሁ፤ ቀደም ሲል እንደ መለከት ሲናገረኝ የሰማሁት ድምፅ፣ “ወደዚህ ና፤ ከዚህም በኋላ ሊሆን የሚገባውን ነገር አሳይሃለሁ” አለኝ።