ሐዋርያት ሥራ 7:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የነገድ አባቶችም በዮሴፍ ቀንተው በባርነት ወደ ግብጽ ሸጡት፤ እግዚአብሔር ግን ከርሱ ጋራ ስለ ነበር፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የአባቶችም አለቆች በዮሴፍ ቀንተው ወደ ግብጽ ሸጡት፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የያዕቆብ ልጆች በወንድማቸው በዮሴፍ ላይ ቀንተው በግብጽ አገር ባሪያ እንዲሆን ሸጡት፤ እግዚአብሔር ግን ከእርሱ ጋር ነበረ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የቀደሙ አባቶችም በዮሴፍ ላይ ቀንተው ወደ ግብፅ ሀገር ሸጡት፤ እግዚአብሔር ግን ከእርሱ ጋር ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአባቶችም አለቆች በዮሴፍ ቀንተው ወደ ግብፅ ሸጡት፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ፥ |
ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤትና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ፣ እግዚአብሔር የግብጻዊውን ቤት ባረከ፤ የእግዚአብሔርም በረከት በግቢም በውጭም ባለው የጲጥፋራ ሀብት ንብረት ሁሉ ላይ ሆነ።
ዮሴፍም ወንድሞቹን፣ “እስኪ ወደ እኔ ቀረብ በሉ” አላቸው፤ ወደ እርሱም በቀረቡ ጊዜ እንዲህ አለ፤ “ወደ ግብጽ የሸጣችሁኝ ወንድማችሁ እኔ ዮሴፍ ነኝ፤
በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ፣ ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤ ወንዙን ስትሻገረው፣ አያሰጥምህም፤ በእሳት ውስጥ ስትሄድ፣ አያቃጥልህም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘አሁን ግን ዘሩባቤል ሆይ፤ በርታ፤ የሊቀ ካህናቱ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ፤ በርታ፤ እናንተም የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ በርቱ’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘እኔ ከእናንተ ጋራ ነኝና ሥሩ’ ይላል ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር፤