ሐዋርያት ሥራ 7:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የግዝረትን ኪዳን ሰጠው፤ አብርሃምም ይሥሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው። ይሥሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የነገድ አባቶች ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ እንዲሁም ይስሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የአባቶችን አለቆች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ ስለዚህ አብርሃም ይስሐቅን በወለደ ጊዜ በስምንተኛው ቀን ገረዘው፤ እንዲሁም ይስሐቅ ልጁን ያዕቆብን ገረዘው። ያዕቆብም የነገድ አባቶች የሆኑትን ዐሥራ ሁለቱን ልጆቹን ገረዘ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የግዝረትንም ኪዳን ሰጠው፤ ከዚህም በኋላ ይስሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛው ቀንም ገረዘው፤ እንዲሁ ይስሐቅም ያዕቆብን፥ ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የቀደሙ አባቶችን ገረዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ እንዲሁም ይስሐቅን ወለደ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው ይስሐቅም ያዕቆብን ያዕቆብም አሥራ ሁለቱን የአባቶችን አለቆች። |
“ወንድሞች ሆይ፤ ከቀደምት አባቶች ዳዊት ሞቶ እንደ ተቀበረ፣ መቃብሩም እስከ ዛሬ ድረስ በመካከላችን እንደሚገኝ በድፍረት መናገር እችላለሁ።
ወንድሞች ሆይ፤ ከሰው ዕለታዊ ሕይወት የተለመደውን ምሳሌ አድርጌ ላቅርብ፤ የሰው ኪዳን እንኳ አንድ ጊዜ ከጸደቀ በኋላ ማንም ሊሽረው ወይም በርሱ ላይ ሊጨምርበት እንደማይችል ሁሉ፣ በዚህም ጕዳይ ቢሆን እንደዚሁ ነው።
የምለው እንዲህ ነው፦ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ሕግ፣ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የጸናውን ኪዳን አፍርሶ የተስፋውን ቃል አይሽርም።