ሐዋርያት ሥራ 7:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሊቀ ካህናቱም፣ “ይህ የቀረበብህ ክስ እውነት ነውን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሊቀ ካህናቱም “ይህ ነገር እንዲህ ነውን?” አለው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የካህናት አለቃው እስጢፋኖስን “ይህ የተባለው ነገር ልክ ነውን?” ሲል ጠየቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊቀ ካህናቱም፥ “በእውነት እንዲህ ብለሃልን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሊቀ ካህናቱም፦ “ይህ ነገር እንዲህ ነውን?” አለው፤ |
እስጢፋኖስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ወንድሞችና አባቶች ሆይ፤ አድምጡኝ! አባታችን አብርሃም ወደ ካራን ከመምጣቱ በፊት፣ ገና በመስጴጦምያ ሳለ፣ የክብር አምላክ ተገልጦለት፣