2 ሳሙኤል 5:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ፤ አርባ ዓመትም ገዛ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ፤ አርባ ዓመትም ገዛ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት በነገሠበት ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር፤ በጠቅላላ የነገሠበት ዘመን አርባ ዓመት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሠላሳ ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ አርባ ዓመትም ነገሠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሠላሳ ዓመት ልጅ ነበረ፥ አርባ ዓመትም ነገሠ። |
በኬብሮናውያን በኩል በቤተ ሰቦቻቸው የትውልድ መዝገብ መሠረት ይሪያ አለቃቸው ነበረ። በዳዊት ዘመነ መንግሥት በአርባኛው ዓመት መዛግብቱ ተመርምረው ስለ ነበር፣ በገለዓድ ውስጥ ኢያዜር በተባለ ቦታ ከኬብሮናውያን መካከል ጠንካራ ሰዎች ሊገኙ ችለዋል።