2 ሳሙኤል 24:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ጠቅላላ ቍጥር ለንጉሡ አሳወቀ፤ በእስራኤል ስምንት መቶ ሺሕ፣ በይሁዳ ዐምስት መቶ ሺሕ ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ብቃት ያላቸው ሰዎች ተገኙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአብም የሕዝቡን ጠቅላላ ቍጥር ለንጉሡ አሳወቀ፤ በእስራኤል ስምንት መቶ ሺህ፥ በይሁዳ አምስት መቶ ሺህ ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ብቃት ያላቸው ሰዎች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብም በእስራኤል ስምንት መቶ ሺህ፥ በይሁዳ አምስት መቶ ሺህ በውትድርና ለማገልገል ብቃት ያላቸው ሰዎች መኖራቸውንም ለንጉሡ አሳወቀ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም የሕዝቡን ቍጥር ድምር ለንጉሡ ሰጠ፤ በእስራኤልም ሰይፍ የሚመዝዙ ስምንት መቶ ሺህ ጽኑዓን ሰዎች ነበሩ፤ የይሁዳም ተዋጊዎች ሰዎች አምስት መቶ ሺህ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም የሕዝቡን ቍጥር ድምር ለንጉሡ ሰጠ፥ በእስራኤልም ሰይፍ የሚመዝዙ ስምንት መቶ ሺህ ጽኑዓን ሰዎች ነበሩ፥ የይሁዳም ሰዎች አምስት መቶ ሺህ ነበሩ። |
ከይሁዳ ዝርያ፦ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።