ኢዮአብ ግን ንጉሡን፣ “አምላክህ እግዚአብሔር ሰራዊቱን በመቶ ዕጥፍ ያብዛው፤ የጌታዬ የንጉሡ ዐይን ይህን ለማየት ይብቃ፤ ንጉሡ ጌታዬ ግን ይህን ለማድረግ የፈለገው ለምንድን ነው?” ሲል መለሰለት።
2 ሳሙኤል 24:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆኖም የንጉሡ ቃል ኢዮአብንና የሰራዊቱን አዛዦች ስላሸነፋቸው፣ የእስራኤልን ሰራዊት ለመመዝገብ ከፊቱ ወጥተው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሆኖም የንጉሡ ቃል ኢዮአብንና የሠራዊቱን አዛዦች አሸነፋቸው፤ ስለዚህ የእስራኤልን ሕዝብ ለመቁጠር ከፊቱ ወጥተው ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ ግን ኢዮአብና የጦር መኰንኖቹ ትእዛዙን እንዲፈጽሙ ስላስገደዳቸው ከፊቱ ወጥተው የእስራኤልን ሕዝብ ለመቊጠር ሄዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን የንጉሡ ቃል በኢዮአብና በሠራዊቱ አለቆች ላይ አሸነፈ። ኢዮአብና የሠራዊቱ አለቆችም የእስራኤልን ሕዝብ ይቈጥሩ ዘንድ ከንጉሥ ዘንድ ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን የንጉሡ ቃል በኢዮአብና በሠራዊቱ አለቆች ላይ አሸነፈ። ኢዮአብና የሠራዊቱ አለቆችም የእስራኤልን ሕዝብ ይቆጥሩ ዘንድ ከንጉሥ ዘንድ ወጡ። |
ኢዮአብ ግን ንጉሡን፣ “አምላክህ እግዚአብሔር ሰራዊቱን በመቶ ዕጥፍ ያብዛው፤ የጌታዬ የንጉሡ ዐይን ይህን ለማየት ይብቃ፤ ንጉሡ ጌታዬ ግን ይህን ለማድረግ የፈለገው ለምንድን ነው?” ሲል መለሰለት።
ዮርዳኖስን ከተሻገሩ በኋላ፣ በሸለቆው ውስጥ ካለችው ከተማ በስተ ደቡብ በምትገኘው በአሮዔር አጠገብ ሰፈሩ፤ ከዚያም በጋድ በኩል አድርገው ወደ ኢያዜር ሄዱ፤
“የእስራኤላውያንን ጠቅላላ ቈጠራ በምታደርግበት ጊዜ እያንዳንዱ ሰው በሚቈጠርበት ወቅት ለሕይወቱ ቤዛ የሚሆን ወጆ ለእግዚአብሔር መክፈል አለበት፤ በዚህም ዐይነት ስትቈጥራቸው በእነርሱ ላይ መቅሠፍት አይመጣም።