2 ሳሙኤል 19:34 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤርዜሊ ግን ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ከንጉሡ ጋራ ወደ ኢየሩሳሌም የምሄደው ለየትኛው ዕድሜዬ ብዬ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ባርዚላይ፥ “ከእኔ ጋር ተሻገርና በኢየሩሳሌም አብረኸኝ ኑር፤ የሚያስፈልግህን እኔ አደርግልሃለሁ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባርዚላይ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ንጉሥ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲያ ብዙ ዘመን አልኖርም፤ ታዲያ፥ ከአንተ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ ምን ያስፈልገኛል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤርዜሊም ንጉሡን አለው፥ “ከንጉሡ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም እወጣ ዘንድ ከሕይወቴ ዘመን ምን ያህል ቀረኝ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤርዜሊም ንጉሡን አለው፦ ከንጉሡ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም እወጣ ዘንድ ከሕይወቴ ዘመን ምን ያህል ቀረኝ? |