2 ሳሙኤል 19:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ገለዓዳዊው ቤርዜሊ ከሮግሊም ወረደ፤ ንጉሡን ለመሸኘትም ዐብሮት ዮርዳኖስን ተሻገረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መፊቦሼትም ንጉሡን፥ “ንጉሥ ጌታዬ እንኳን በደኅና ተመለሰ እንጂ፥ እርሱ ሁሉንም ይውሰደው” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገለዓዳዊው ባርዚላይ ንጉሡን አጅቦ የዮርዳኖስን ወንዝ ለመሻገር ከሮገሊም መጣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገለዓዳዊውም ቤርዜሊ ከሮግሊም ወረደ፤ በዮርዳኖስም ሊሸኘው ከንጉሡ ጋር ዮርዳኖስን ተሻገረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገለዓዳዊውም ቤርዜሊ ከሮግሊም ወረደ፥ ሊሸኘውም ከንጉሡ ጋር ዮርዳኖስን ተሻገረ። |
“ከወንድምህ ከአቤሴሎም በሸሸሁ ጊዜ መልካም ነገር አድርገውልኛልና ለገለዓዳዊው ለቤርዜሊ ልጆች ግን በጎ ነገር አድርግላቸው፤ ማእድህን ከሚካፈሉ ሰዎችም ጋራ ዐብረው ይብሉ።