ወንድሟ አቤሴሎምም፣ “ያ ወንድምሽ አምኖን ካንቺ ጋራ ነበርን? እኅቴ ሆይ፣ አሁን ዝም በዪ፤ ወንድምሽ ስለ ሆነ፤ ነገሩን በልብሽ አትያዢው” አላት። ትዕማርም በወንድሟ በአቤሴሎም ቤት ብቸኛ ሴት ሆና ኖረች።
2 ሳሙኤል 19:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ በደሌን አይቍጠርብኝ፤ ንጉሥ ጌታዬ ከኢየሩሳሌም በወጣህባት ዕለት የፈጸምሁትን ስሕተት እርሳው፤ ከአእምሮህም አውጣው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንጉሡን ቤተሰብ ለማምጣትና እርሱ የሚፈልገውንም ሁሉ ለማድረግ ዮርዳኖስን ተሻገሩ። የጌራ ልጅ ሳሚ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ በንጉሡም ፊት ተደፍቶ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ንጉሥ ሆይ! ከኢየሩሳሌም ወጥተህ በሄድክበት ቀን ያደረግኹትን በደል እባክህ ይቅር በለኝ፤ ቂም በቀልም አትያዝብኝ፤ ዳግመኛም ስለ እርሱ አታስብ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ንጉሡን አለው፥ “ጌታዬ! ኀጢአቴን አትቍጠርብኝ፤ ጌታዬ ንጉሡ ከኢየሩሳሌም በወጣህ ቀን ባሪያህ የበደልሁህን አታስብብኝ፤ ጌታዬ ንጉሡም በልብህ አታኑርብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡንም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ኃጢአቴን አትቍጠርብኝ፥ ጌታዬ ንጉሡ፥ ከኢየሩሳሌም በወጣህ ቀነ ባሪያህ የበደልሁህን አታስብብኝ፥ ንጉሡም በልቡ አያኑረው። |
ወንድሟ አቤሴሎምም፣ “ያ ወንድምሽ አምኖን ካንቺ ጋራ ነበርን? እኅቴ ሆይ፣ አሁን ዝም በዪ፤ ወንድምሽ ስለ ሆነ፤ ነገሩን በልብሽ አትያዢው” አላት። ትዕማርም በወንድሟ በአቤሴሎም ቤት ብቸኛ ሴት ሆና ኖረች።
የንጉሡን ቤተ ሰው ለማምጣትና እርሱ የሚፈልገውንም ሁሉ ለማድረግ በመልካው ተሻገሩ። የጌራ ልጅ ሳሚ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ በንጉሡም ፊት ተደፍቶ፣
ከእንግዲህ ማንም ሰው ባልንጀራውን፣ ወይም ወንድሙን፣ ‘እግዚአብሔርን ዕወቅ’ ብሎ አያስተምርም፤ ከትንሹ ጀምሮ እስከ ትልቁ፣ ሁሉም እኔን ያውቁኛልና፤” ይላል እግዚአብሔር። “በደላቸውን ይቅር እላለሁ፤ ኀጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስብም።”
ስለ እርሱ እግዚአብሔርን ስጠይቅስ ያ ቀን የመጀመሪያ ጊዜዬ ነበርን? ፈጽሞ አልነበረም፤ ይህን ጕዳይ በተመለከተ አገልጋይህ የሚያውቀው ምንም ነገር ስለሌለ ንጉሥ እኔን አገልጋዩን ወይም ከአባቴ ቤተ ሰብ ማንንም ጥፋተኛ አያድርግ።”
ጌታዬ፣ ያን ምናምንቴ ሰው ናባልን ከቁም ነገር አይቍጠረው፤ ስሙ ራሱ ሞኝ ማለት ስለ ሆነ፣ ሰውየውም ልክ እንደ ስሙ ነው፤ ሞኝነትም ዐብሮት የኖረ ነው። እኔ አገልጋይህ ግን ጌታዬ የላካቸውን ጕልማሶች አላየኋቸውም።
ሳኦልም፣ “በድያለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ፤ ተመለስ፤ ዛሬ ነፍሴ በፊትህ ስለ ከበረች፣ ከእንግዲህ ወዲያ አልጐዳህም፤ በርግጥ የሞኝ ሥራ ሠርቻለሁ፤ እጅግ ሲበዛም ተሳስቻለሁ” አለ።