2 ሳሙኤል 19:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ዳዊት ወደ ካህናቱ ወደ ሳዶቅና ወደ አብያታር እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፤ “የይሁዳ ሽማግሌዎችን እንዲህ በሏቸው አለ፤ ‘በመላው እስራኤል የሚባለው ሁሉ ለንጉሡ ባለበት የደረሰው ስለ ሆነ፣ ንጉሡን ወደ ቤተ መንግሥቱ ለመመለስ እንዴት የመጨረሻ ሰዎች ትሆናላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በላያችን ሆኖ እንዲገዛን የቀባነው አቤሴሎም ደግሞ በጦርነት ሞቷል፤ ታዲያ ስለ ንጉሡ የመመለስ ጉዳይ ለምንድን ነው ዝም የምትሉት?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ዳዊትም እስራኤላውያን እርስ በርሳቸው የተናገሩትን ሰማ፤ ስለዚህም ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን በመላክ የይሁዳን መሪዎች እንዲህ ብለው እንዲጠይቁአቸው አዘዘ፤ “ንጉሡን ረድታችሁ ወደ ቤተ መንግሥቱ ለመመለስ ስለምን እናንተ የመጨረሻዎቹ ትሆናላችሁ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡ ዳዊትም ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር ልኮ እንዲህ አላቸው፥ “ለይሁዳ ሽማግሌዎች እንዲህ ብላችሁ ተናገሩአቸው፦ የእስራኤል ሁሉ ነገር ወደ ንጉሡ ደርሶአልና ንጉሡን ወደ ቤቱ ከመመለስ ስለምን ዘገያችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ዳዊት ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር ልኮ እንዲህ አላቸው፦ ለይሁዳ ሽማግሌዎች እንዲህ ብላችሁ ተናገሩአቸው፦ የእስራኤል ሁሉ ነገር ወደ ንጉሡ ደርሶአልና ንጉሡን ወደ ቤቱ ከመመለስ ስለ ምን ዘገያችሁ? |
ኢዮአብም፣ “ከእንግዲህ በዚህ ሁኔታ ከአንተ ጋራ ጊዜ ማጥፋት አልችልም” አለው፤ ስለዚህ በእጁ ሦስት ጦር ይዞ ሄደና አቤሴሎም እዛፉ ላይ ተንጠልጥሎ ገና በሕይወት እያለ፣ ወርውሮ በልቡ ላይ ተከላቸው።
ወዲያውም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ መጥተው፣ “ወንድሞቻችን የይሁዳ ሰዎች ንጉሡን በሹልክታ ለብቻቸው ይዘው እርሱንና ቤተ ሰውን ከተከታዮቹ ጋራ ዮርዳኖስን ለምን አሻገሩ?” አሉት።
ስለዚህ እኛ የክርስቶስ እንደራሴዎች ነን፤ እግዚአብሔርም በእኛ አማካይነት ጥሪውን ያቀርባል፤ እኛም ከእግዚአብሔር ጋራ ታረቁ ብለን በክርስቶስ እንለምናችኋለን።