አባትህ ታላቅ ጦረኛ፣ ዐብረውት ያሉትም ጀግኖች መሆናቸውን እስራኤል ሁሉ ስለሚያውቅ፣ ልቡ እንደ አንበሳ ልብ ነው የተባለው ደፋሩ ወታደር እንኳ በፍርሀት ይርዳል።
2 ሳሙኤል 17:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ አሁን እንኳ በአንዱ ዋሻ ወይም በሌላ ቦታ ተደብቆ ይሆናል። እርሱ ቀድሞ አደጋ በመጣል ከሰዎችህ ጥቂት ቢሞቱ ይህን የሰማ ሁሉ፣ ‘አቤሴሎምን የተከተለው ሰራዊት ዐለቀ’ ብሎ ያወራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ አሁን እንኳ በአንዱ ዋሻ ወይም በሌላ ቦታ ተደብቆ ይሆናል። ጥቂት ሰዎች በመጀመሪያ በሚጥልባቸው ጥቃት ቢሞቱ ይህን የሰማ ሁሉ፥ ‘አቤሴሎምን የተከተለው ሠራዊት ተፈጀ’ ብሎ ያወራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምናልባት አሁን እንኳ በዋሻ ውስጥ ወይም በሌላ ስፍራ ተሸሽጎ ሊሆን ይችላል፤ ዳዊት በአንተ ሠራዊት ላይ አደጋ እንደ ጣለባቸው የሚሰማ ሰው ሁሉ ወዲያውኑ ወታደሮችህ እንደ ተሸነፉ አድርጎ ያወራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተራራው ላይ፥ ያም ባይሆን በአንድ ቦታ ተሰውሮአልና ከእነርሱ ፊተኞቹ ቢወድቁ የሚሰማው ሁሉ አቤሴሎምን የተከተለ ሕዝብ ተመታ ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ምናልባት በአንድ ጉድጓድ ወይም በማናቸውም ስፍራ ተሸሽጎ ይሆናል፥ በመጀመሪያም ከእነርሱ አያሌዎች ቢወድቁ፥ የሚሰማው ሁሉ፦ አቤሴሎምን የተከተለው ሕዝብ ተመታ ይላል። |
አባትህ ታላቅ ጦረኛ፣ ዐብረውት ያሉትም ጀግኖች መሆናቸውን እስራኤል ሁሉ ስለሚያውቅ፣ ልቡ እንደ አንበሳ ልብ ነው የተባለው ደፋሩ ወታደር እንኳ በፍርሀት ይርዳል።
አባትህና ሰዎቹ የማይበገሩ ተዋጊዎችና ግልገሎቿ እንደ ተነጠቁባት የዱር ድብ አስፈሪ መሆናቸውን አንተም ታውቃለህ፤ በተጨማሪም አባትህ በቂ ልምድ ያለው ነው፤ ሌሊቱን ከሰራዊቱ ጋራ አያድርም፤
እስማኤል ከጎዶልያስ በተጨማሪ የገደላቸው ሰዎች ሁሉ ሬሳ የተጣለበት የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓድ፣ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ስለ ፈራ ለመከላከል ያሠራው ነበር፤ ይህን ጕድጓድ የናታንያ ልጅ እስማኤል በሬሳ ሞላው።
የጋይም ሰዎች እስራኤላውያንንም ከከተማዪቱ ቅጥር በር ጀምሮ እስከ ሽባሪም ድረስ በማባረር ቍልቍለቱ ላይ መቷቸው፤ ከእነርሱም ሠላሳ ስድስት ያህል ሰው ገደሉባቸው። ከዚህ የተነሣም የሕዝቡ ልብ ቀለጠ፤ እንደ ውሃም ፈሰሰ።
እነርሱም፣ ‘ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት አሁንም ከእኛ በመሸሽ ላይ ናቸው’ በማለት ከከተማዪቱ እስክናርቃቸው ድረስ ይከታተሉናል፤ በዚህ ሁኔታ እኛም እንሸሻለን፤
ሳኦልም በመንገድ ዳር ወዳለው ወደ አንድ የበጎች ማደሪያ በደረሰ ጊዜ፣ ዋሻ አግኝቶ ወገቡን ሊሞክር ወደዚያ ገባ። ዳዊትና ሰዎቹም ከዋሻው በውስጠኛው ቦታ ተቀምጠው ነበር።