አንተ የአንበሳ ደቦል ይሁዳ፤ ከዐደንህ የምትመለስ ልጄ፣ እንደ አንበሳ ያደፍጣል፤ በምድርም ላይ ይተኛል፤ እንደ እንስት አንበሳም ያደባል፤ ታዲያ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል?
2 ሳሙኤል 17:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባትህ ታላቅ ጦረኛ፣ ዐብረውት ያሉትም ጀግኖች መሆናቸውን እስራኤል ሁሉ ስለሚያውቅ፣ ልቡ እንደ አንበሳ ልብ ነው የተባለው ደፋሩ ወታደር እንኳ በፍርሀት ይርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባትህ ታላቅ ጦረኛ፥ አብረውት ያሉትም ጀግኖች መሆናቸውን እስራኤል ሁሉ ስለሚያውቅ፥ ልቡ እንደ አንበሳ ልብ የሚደፍረው እንኳ በፍርሀት ይርዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባትህ ታላቅ ጦረኛ መሆኑንና የእርሱም ተከታዮች ብርቱ ተዋጊዎች መሆናቸውን በእስራኤል የሚኖር ሁሉ ስለሚያውቅ እንደ አንበሳ ደፋሮች የሆኑት ወታደሮችህ እንኳ ልባቸው በፍርሃት ሊቀልጥ ይችላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ኀይለኛ ሰው ነውና፥ ልቡም እንደ አንበሳ ልብ ፈጽሞ ይናደዳልና፤ እስራኤልም ሁሉ አባትህ ጽኑዕ፥ ከእርሱም ጋር ያሉት ስዎች ኀያላን እንደ ሆኑ ያውቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም ሁሉ አባትህ ኃያል እንደ ሆነ፥ ከእርሱም ጋር ያሉት ሰዎች ጽኑዓን እንደ ሆኑ ያውቃልና ጽኑዕ ልቡም እንደ አንበሳ ልብ የሆነው ፈጽሞ ይቀልጣል። |
አንተ የአንበሳ ደቦል ይሁዳ፤ ከዐደንህ የምትመለስ ልጄ፣ እንደ አንበሳ ያደፍጣል፤ በምድርም ላይ ይተኛል፤ እንደ እንስት አንበሳም ያደባል፤ ታዲያ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል?
ሳኦልና ዮናታን በሕይወት እያሉ፣ የሚዋደዱና የሚስማሙ ነበሩ፤ ሲሞቱም አልተለያዩም፤ ከንስርም ይልቅ ፈጣኖች፣ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ።
እነሆ፤ አሁን እንኳ በአንዱ ዋሻ ወይም በሌላ ቦታ ተደብቆ ይሆናል። እርሱ ቀድሞ አደጋ በመጣል ከሰዎችህ ጥቂት ቢሞቱ ይህን የሰማ ሁሉ፣ ‘አቤሴሎምን የተከተለው ሰራዊት ዐለቀ’ ብሎ ያወራል።
የቀብጽኤል አገር ሰው የሆነው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ታላቅ ጀብዱ የሠራ ሌላው ጐበዝ ተዋጊ ነበረ፤ እርሱም ሁለት በጣም የታወቁ የሞዓብ ሰዎችን ገደለ፤ እንዲሁም በረዶ በጣለበት ዕለት በጕድጓድ ውስጥ ገብቶ አንበሳ ገድሏል፤
በዚያ ጊዜ በራእይ ተናገርህ፤ ታማኝ ሕዝብህንም እንዲህ አልህ፤ “ኀያሉን ሰው ሥልጣን አጐናጸፍሁት፤ ከሕዝብ መካከል የተመረጠውንም ከፍ ከፍ አደረግሁት።
ስለ ግብጽ የተነገረ ንግር፤ እነሆ፤ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ላይ ተቀምጦ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽ ጣዖቶች በፊቱ ይርዳሉ፤ የግብጻውያንም ልብ በውስጣቸው ይቀልጣል።
ልብ ሁሉ ይቀልጥ ዘንድ፣ የሚወድቁትም እንዲበዙ፣ በበሮቻቸው ሁሉ፣ የግድያውን ሰይፍ አኑሬአለሁ። ወዮ! እንዲያብረቀርቅ ተወልውሏል፤ ለመግደልም ተመዝዟል።
ታዲያ ወዴት መሄድ እንችላለን? ወንድሞቻችን፣ ‘ሰዎቹ ከእኛ ይልቅ ብርቱዎችና ቁመተ ረዣዥሞች፣ ከተሞቹም ትልልቆችና እስከ ሰማይ በሚደርስ ቅጥር የታጠሩ ናቸው፤ እንዲያውም በዚያ የዔናቅን ልጆች አይተናቸዋል’ ሲሉ እንድንፈራ አድርገውናል።”
ከአገልጋዮቹም አንዱ፣ “መልካም አድርጎ በገና መደርደር የሚችለውን የቤተ ልሔሙን የእሴይን ልጅ አይቻለሁ፣ እርሱም ጀግናና ተዋጊ ነው፤ በአነጋገሩ አስተዋይና የደስ ደስ ያለው ነው፤ እግዚአብሔርም ከርሱ ጋራ ነው” ብሎ መለሰ።
ሳኦል ዳዊትን፣ “ታላቋ ልጄ ሜሮብ እነኋት፤ እርሷን እድርልሃለሁ፤ አንተ ግን በጀግንነት አገልግለኝ፤ የእግዚአብሔርንም ጦርነቶች ተዋጋ” አለው፤ ሳኦል በልቡ፣ “ፍልስጥኤማውያን እጃቸውን ያንሡበት እንጂ እኔ በርሱ ላይ እጄን አላነሣም” ብሎ ነበርና።