La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 8:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከሰባት ዓመት በኋላም፣ ከፍልስጥኤም ምድር ተመልሳ መጣች፤ ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ አቤቱታ ለማቅረብም ወደ ንጉሡ ሄደች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከሰባቱም የራብ ዓመቶች ፍጻሜ በኋላ ወደ እስራኤል ተመለሰች፤ መኖሪያ ቤትዋና የእርሻ መሬትዋ እንዲመለስላት ለመጠየቅ ወደ ንጉሡ ቀረበች።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከሰባቱም የራብ ዓመቶች ፍጻሜ በኋላ ወደ እስራኤል ተመለሰች፤ መኖሪያ ቤትዋና የእርሻ መሬትዋ እንዲመለስላት ለመጠየቅ ወደ ንጉሡ ቀረበች።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሰባ​ቱም ዓመት ካለፈ በኋላ ያች ሴት ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሀገር ተመ​ለ​ሰች፤ ሄዳም ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ልት​ጮህ ወደ ንጉሡ ወጣች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሰባቱም ዓመት በተፈጸመ ጊዜ ሴቲቱ ከፍልስጥኤም አገር ተመለሰች፤ ስለ ቤትዋና ስለ መሬትዋ ልትጮኽ ወደ ንጉሡ ወጣች።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 8:3
10 Referencias Cruzadas  

የቴቁሔዪቱም ሴት ወደ ንጉሡ ገብታ፣ በንጉሡ ፊት ወደ መሬት በግምባሯ ተደፍታ እጅ በመንሣት አክብሮቷን ከገለጠች በኋላ፣ “ንጉሥ ሆይ! እርዳኝ” አለች።


ኤልሳዕም፣ “ ‘ለእኛ ስትይ በጣም ተቸግረሻል፤ ምን እንዲደረግልሽ ትፈልጊአለሽ? ለንጉሡ ወይስ ለሰራዊቱ አዛዥ የምንነግርልሽ ጕዳይ አለን?’ ብለህ ጠይቃት” አለው። ሴቲቱም መልሳ፣ “እኔ እኮ የምኖረው በገዛ ወገኖቼ መካከል ነው” አለችው።


የእስራኤልም ንጉሥ በቅጥሩ ላይ በሚመላለስበት ጊዜ አንዲት ሴት፣ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ “ጌታዬ፣ ንጉሥ ሆይ፤ እባክህ ርዳኝ!” አለች።


ሴቲቱም ተነሥታ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ነገራት አደረገች፤ ከነቤተ ሰቧም ሄዳ፣ በፍልስጥኤም ምድር ሰባት ዓመት ተቀመጠች።


በዚህ ጊዜ ንጉሡ የእግዚአብሔርን ሰው አገልጋይ ግያዝን፣ “ኤልሳዕ ያደረጋቸውን ታላላቅ ሥራዎች ሁሉ እስኪ ንገረኝ” እያለው ነበር።


ንጉሡም ስለ ስለዚሁ ጕዳይ ጠየቃትና ነገረችው። ከዚያም ንጉሡ፣ “የነበራትን ሁሉ እንዲሁም ትታ ከሄደችበት ጊዜ አንሥቶ እስካሁን ድረስ ያለውን የዕርሻዋን ሰብል በሙሉ እንድትመልስላት” ሲል አንድ ሹም አዘዘላት።


የድኾችንና የችግረኞችን ፍትሕ አላጓደለም፤ ስለዚህም ሁሉ መልካም ሆነለት። እኔን ማወቅ ማለት ይህ አይደለምን?” ይላል እግዚአብሔር።


የኖረችበትን ስፍራ ትታ ከሁለቱ ምራቶቿ ጋራ ወደ ይሁዳ ምድር የሚመልሳቸውን መንገድ ይዘው ጕዟቸውን ቀጠሉ።