2 ነገሥት 8:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤልሳዕም፣ “ሂድና፣ ‘መዳኑንስ በርግጥ ትድናለህ’ በለው፤ ነገር ግን እንደሚሞት እግዚአብሔር ገልጾልኛል” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልሳዕም “ቤንሀዳድ እንደሚሞት እግዚአብሔር ገልጦልኛል፤ አንተ ግን ትድናለህ ብለህ ንገረው” አለው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልሳዕም “ቤንሀዳድ እንደሚሞት እግዚአብሔር ገልጦልኛል፤ አንተ ግን ትድናለህ ብለህ ንገረው” አለው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልሳዕም፥ “ሂድ፥ መዳንስ ትድናለህ በለው፤ ነገር ግን እንዲሞት እግዚአብሔር አሳይቶኛል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤልሳዕም “ሂድ፤ ‘መዳንስ ትድናለህ፤’ በለው፤ ነገር ግን እንዲሞት እግዚአብሔር አሳይቶኛል፤” አለው። |
ወደ ንጉሡ በመጣ ጊዜ ንጉሡ፣ “ሚክያስ ሆይ፤ በገለዓድ በምትገኘው ራሞት ላይ እንዝመት ወይስ እንቅር?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “ሂዱና ድል አድርጉ እግዚአብሔር በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል” ብሎ መለሰለት።
ንጉሡንም፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለመሆኑ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ስለ ራስህ ለመጠየቅ መልእክተኞች የላክኸው በእስራኤል አምላክ ስለሌለ ነውን? ይህን በማድረግህም ከተኛህበት ዐልጋ ፈጽሞ አትነሣም፤ በርግጥ ትሞታለህ’ ” ብሎ ነገረው።
በዐራጣ ቢያበድር፤ ከፍተኛ ወለድም ቢቀበል፣ እንዲህ ዐይነቱ ሰው በሕይወት ይኖራልን? ከቶ አይኖርም! እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች አድርጓልና በርግጥ ይሞታል፤ ደሙም በገዛ ራሱ ላይ ይሆናል።
ጌታ እግዚአብሔር ይህን አሳየኝ፤ የንጉሡ የመኸር እህል ከተሰበሰበ በኋላ ገቦው መብቀል በጀመረ ጊዜ፣ እርሱ የአንበጣ መንጋ እንዲፈለፈል አደረገ።