በዚህ ጊዜ ንዕማን የሶርያ ንጉሥ ጦር አዛዥ ነበረ፤ እግዚአብሔር በዚህ ሰው አማካይነት፣ ሶርያ ድልን እንድትጐናጸፍ ስላደረጋት በጌታው ዘንድ ታላቅና የተከበረ ሰው ነበር። ጀግና ወታደር ቢሆንም ለምጽ ወጥቶበት ነበር።
2 ነገሥት 7:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የሚያሠቅቅ የቈዳ በሽታ የያዛቸው አራት ሰዎች በከተማዪቱ መግቢያ በር አጠገብ ነበሩ፤ እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “እስክንሞት ድረስ በዚህ የምንቈየው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውነታቸው የቆዳ በሽታ የያዛቸው አራት ሰዎች ከሰማርያ ቅጽር በር ውጪ ነበሩ፤ እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “እስክንሞት ድረስ ስለምን በዚህ እንቆያለን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውነታቸው የቆዳ በሽታ የያዛቸው አራት ሰዎች ከሰማርያ ቅጽር በር ውጪ ነበሩ፤ እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “እስክንሞት ድረስ ስለምን በዚህ እንቈያለን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በከተማዋም በር አራት ለምጻሞች ሰዎች ነበሩ፤ እርስ በርሳቸውም፥ “እስክንሞት ድረስ በዚህ ለምን እንቀመጣለን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በበሩም መግቢያ አራት ለምጻም ሰዎች ነበሩ፤ እርስ በርሳቸውም “እስክንሞት ድረስ በዚህ ለምን እንቀመጣለን? |
በዚህ ጊዜ ንዕማን የሶርያ ንጉሥ ጦር አዛዥ ነበረ፤ እግዚአብሔር በዚህ ሰው አማካይነት፣ ሶርያ ድልን እንድትጐናጸፍ ስላደረጋት በጌታው ዘንድ ታላቅና የተከበረ ሰው ነበር። ጀግና ወታደር ቢሆንም ለምጽ ወጥቶበት ነበር።
ታዲያ፣ ‘ወደ ከተማዪቱ እንግባ ብንል’ በዚያም ራብ ስላለ እንሞታለን፤ በዚሁም ብንሆን ያው መሞታችን አይቀርም፤ ስለዚህ ወደ ሶርያውያኑ ሰፈር ዝም ብለን እንሂድ፤ ዝም ካሉን ሕይወታችን ትተርፋለች፤ ከገደሉንም ሞቶ መገላገል ነው።”
ለምን እዚህ እንቀመጣለን? በአንድነት ተሰብሰቡ! ወደ ተመሸጉት ከተሞች እንሽሽ፤ በዚያም እንጥፋ! በርሱ ላይ ኀጢአትን ስላደረግን፣ እግዚአብሔር አምላካችን እንድንጠፋ አድርጎናል፤ የተመረዘ ውሃ እንድንጠጣ ሰጥቶናል።
ደመናው ከድንኳኑ ላይ በተነሣ ጊዜ፣ እነሆ፤ ማርያም በለምጽ ተመታች፤ እንደ በረዶም ነጣች። አሮንም ወደ እርሷ ዘወር ሲል ለምጽ ወርሷት አየ፤
እግዚአብሔርም ለሙሴ፣ “አባቷ እፊቷ ላይ ቢተፋባት እስከ ሰባት ቀን በኀፍረት መቈየት አይገባትምን? አሁንም ከሰፈር ውጭ ሰባት ቀን እንድትገለል አድርግ፤ ከዚያ በኋላ ግን ልትመለስ ትችላለች” ሲል መለሰለት።