2 ነገሥት 7:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ታዲያ፣ ‘ወደ ከተማዪቱ እንግባ ብንል’ በዚያም ራብ ስላለ እንሞታለን፤ በዚሁም ብንሆን ያው መሞታችን አይቀርም፤ ስለዚህ ወደ ሶርያውያኑ ሰፈር ዝም ብለን እንሂድ፤ ዝም ካሉን ሕይወታችን ትተርፋለች፤ ከገደሉንም ሞቶ መገላገል ነው።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ወደ ከተማይቱ መግባት ምንም ጥቅም የለውም፤ እዚያ ከገባን በራብ እንሞታለን፤ እዚህም ብንቀር ከመሞት አንድንም፤ ስለዚህ ተነሥተን ወደ ሶርያውያን ሰፈር እንሂድ፤ እነርሱም ቢሆኑ ከመግደል የከፋ ሌላ ምንም ነገር ሊያደርጉብን አይችሉም፤ ምናልባትም ሕይወታችንን ያተርፉ ይሆናል።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ወደ ከተማይቱ መግባት ምንም ጥቅም የለውም፤ እዚያ ከገባን በራብ እንሞታለን፤ እዚህም ብንቀር ከመሞት አንድንም፤ ስለዚህ ተነሥተን ወደ ሶርያውያን ሰፈር እንሂድ፤ እነርሱም ቢሆኑ ከመግደል የከፋ ሌላ ምንም ነገር ሊያደርጉብን አይችሉም፤ ምናልባትም ሕይወታችንን ያተርፉ ይሆናል።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ወደ ከተማ ብንገባ ራብ በከተማ አለና፥ በዚያ እንሞታለን፤ በዚህም ብንቀመጥ እንሞታለን። እንግዲህ ኑ፥ ወደ ሶርያውያን ሰፈር እንሂድ፤ በሕይወት ቢያኖሩን እንኖራለን፤ ቢገድሉንም እንሞታለን” ተባባሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ወደ ከተማ እንገባ ዘንድ ብንወድድ ራብ በከተማ አለ፤ በዚያም እንሞታለን፤ በዚህም ብንቀመጥ እንሞታለን። እንግዲህ ኑ፤ ወደ ሶርያውያን ሰፈር እንሽሽ፤ በሕይወት ቢያኖሩን እንኖራለን፤ ቢገድሉንም እንሞታለን፤” ተባባሉ። Ver Capítulo |