2 ነገሥት 16:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አካዝም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ ከእነርሱ ጋራ በዳዊት ከተማ ተቀበረ። ልጁ ሕዝቅያስም በምትኩ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አካዝ ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ሕዝቅያስ ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አካዝ ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ሕዝቅያስ ነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አካዝም እንደ አባቶቹ አንቀላፋ፥ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም ሕዝቅያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ፤ ልጁም ሕዝቅያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ። |
ምናሴም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ “የዖዛ አትክልት” በሚባለው በቤተ መንግሥቱ አትክልት ውስጥ ተቀበረ። ልጁ አሞንም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
በአካዝ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ተግባርና አካሄዱ ሁሉ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፏል።
አካዝ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በኢየሩሳሌምም ከተማ ተቀበረ፤ የተቀበረው ግን በእስራኤል ነገሥታት መካነ መቃብር አልነበረም። ልጁ ሕዝቅያስም በምትኩ ነገሠ።
በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያን፣ በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን እንዲሁም በእስራኤል ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን ወደ ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤
በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል፣ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ ይህ ነው፤