በሾላ ዛፎች ጫፍ ላይ የሰልፍ ጕዞ ድምፅ ስትሰማም፣ እግዚአብሔር የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ለመምታት ቀድሞህ ወጥቷል ማለት ነውና በዚያ ጊዜ በፍጥነት ወደ ፊት ሂድ።”
2 ነገሥት 13:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም፣ “የምሥራቁን መስኮት ክፈት” አለው፤ ከፈተውም፤ ኤልሳዕም፣ “በል አስፈንጥረው” አለው፤ አስፈነጠረውም፤ ከዚያም፣ “የእግዚአብሔር የድል ቀስት! ሶርያ ድል የምትሆንበት ቀስት!” አለ። ኤልሳዕም እንደ ገና “ሶርያውያንንም አፌቅ ላይ ፈጽመህ ድል ታደርጋቸዋለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልሳዕ “የምሥራቁን መስኮት ክፈት” አለ፤ ንጉሡም ከፈተው፤ ኤልሳዕም “ፍላጻውን አስፈንጥር!” አለው፤ ንጉሡም ፍላጻውን እንዳስፈነጠረ ወዲያውኑ ኤልሳዕ፥ “ፍላጻ ነህ፤ በአንተም አማካይነት እግዚአብሔር ሶርያውያንን ድል ያደርጋል፤ ሶርያውያንን ድል እስክትነሣቸው ድረስ በአፌቅ ከተማ ትወጋቸዋለህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልሳዕ “የምሥራቁን መስኮት ክፈት” አለ፤ ንጉሡም ከፈተው፤ ኤልሳዕም “ፍላጻውን አስፈንጥር!” አለው፤ ንጉሡም ፍላጻውን እንዳስፈነጠረ ወዲያውኑ ኤልሳዕ፥ “ፍላጻ ነህ፤ በአንተም አማካይነት እግዚአብሔር ሶርያውያንን ድል ያደርጋል፤ ሶርያውያንን ድል እስክትነሣቸው ድረስ በአፌቅ ከተማ ትወጋቸዋለህ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የምሥራቁንም መስኮት ክፈት” አለ፤ ከፈተውም። ኤልሳዕም፥ “ወርውር” አለው፤ ወረወረውም እርሱም፥ “የእግዚአብሔር መድኀኒት ፍላጻ ነው፤ ከሶርያ የመዳን ፍላጻ ነው፤ እስክታጠፋቸውም ድረስ ሶርያውያንን በአፌቅ ትመታለህ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “የምሥራቁን መስኮት ክፈት፤” አለ፤ ከፈተውም። ኤልሳዕም “ወርውር!” አለ፤ ወረወረውም። እርሱም “የእግዚአብሔር መድኃኒት ፍላጻ ነው፤ በሶርያ ላይ የመድኃኒት ፍላጻ ነው፤ እስክታጠፋቸው ድረስ ሶርያውያንን በአፌቅ ትመታለህ፤” አለ። |
በሾላ ዛፎች ጫፍ ላይ የሰልፍ ጕዞ ድምፅ ስትሰማም፣ እግዚአብሔር የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ለመምታት ቀድሞህ ወጥቷል ማለት ነውና በዚያ ጊዜ በፍጥነት ወደ ፊት ሂድ።”
በየሰፈሩበትም ቦታ ሰባት ቀን ከተፋጠጡ በኋላ በሰባተኛው ቀን ጦርነት ገጠሙ። እስራኤላውያንም በአንዲት ጀምበር ከሶርያውያን ሰራዊት መቶ ሺሕ እግረኛ ገደሉ።
የሳሙኤልም ቃል ወደ እስራኤል ሁሉ ደረሰ። በዚያ ዘመን እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ሊወጉ ወጡ፤ እስራኤላውያን በአቤንኤዘር፣ ፍልስጥኤማውያን ደግሞ በአፌቅ ሰፈሩ።