2 ነገሥት 10:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልእክተኛው እንደ ደረሰም፣ ለኢዩ፣ “የንጉሡን ልጆች ራስ አምጥተዋል” ብሎ ነገረው። ከዚያም ኢዩ፣ “በከተማዪቱ መግቢያ በር ላይ ሁለት ቦታ ከምራችሁ እስከ ነገ ጧት ድረስ አቈዩአቸው” ብሎ አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዩ የአክዓብ ትውልድ ራሶች ተቆርጠው መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ በከተማይቱ ቅጽር በር በሁለት ረድፍ ተከምረው እስከ ተከታዩ ቀን ጧት ድረስ እንዲቆዩ ትእዛዝ ሰጠ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዩ የአክዓብ ትውልድ ራሶች ተቈርጠው መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ በከተማይቱ ቅጽር በር በሁለት ረድፍ ተከምረው እስከ ተከታዩ ቀን ጧት ድረስ እንዲቈዩ ትእዛዝ ሰጠ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልእክተኛም መጥቶ፥ “የንጉሡን ልጆች ራስ ይዘው መጥተዋል” ብሎ ነገረው። ንጉሡም፥ “እስከ ነገ ድረስ በበሩ አደባባይ ሁለት ክምር አድርጋችሁ አኑሩአቸው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልእክተኛም መጥቶ “የንጉሡን ልጆች ራሶች ይዘው መጥተዋል፤” ብሎ ነገረው። እርሱም “እስከ ነገ ድረስ በበሩ አደባባይ ሁለት ክምር አድርጋችሁ አኑሩአቸው፤” አለ። |
ደብዳቤውም በደረሳቸው ጊዜ፣ ሰዎቹ ሰባውን ልዑላን በሙሉ ወስደው ገደሏቸው። ራሳቸውንም በቅርጫት አድርገው ኢዩ ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ላኩ።
በማግስቱም ጧት ኢዩ ወጥቶ በሕዝቡ ሁሉ ፊት በመቆም እንዲህ አለ፤ “እናንተ ንጹሓን ናችሁ፤ ጌታዬን ያሤርሁበትና የገደልሁት እኔ ነኝ። እነዚህን ሁሉ ግን የፈጃቸው ማን ነው?
በድኑን በዕንጨት ላይ እንደ ተሰቀለ አታሳድረው፤ ምክንያቱም በዕንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና፤ አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር እንዳታረክስ፣ በዚያ ዕለት ቅበረው።