እንዲሁም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረጋቸው፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፣ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር። ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት ተገዦች ሆኑ፤ ገበሩለትም።
2 ነገሥት 1:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አክዓብ ከሞተ በኋላ ሞዓብ በእስራኤል ላይ ዐመፀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ከሞተ በኋላ ሞዓብ በእስራኤል ላይ ዐመፀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ከሞተ በኋላ ሞአብ በእስራኤል ላይ ዐመፀ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አክዓብም ከሞተ በኋላ ሞዓብ በእስራኤል ላይ ዐመፀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አክዓብ ከሞተ በኋላ ሞዓብ በእስራኤል ላይ ዐመፀ። |
እንዲሁም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረጋቸው፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፣ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር። ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት ተገዦች ሆኑ፤ ገበሩለትም።
ከዚያም የደማስቆ ክፍል በሆነው የሶርያውያን ግዛት የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ሶርያውያን ተገዙለት፤ ገበሩለትም። እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው።