ጥበበኛ የሆነ እነዚህን ነገሮች ያስተውላል፤ አስተዋይም እነዚህን ነገሮች ይረዳል። የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ነውና፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ዐመፀኞች ግን ይሰናከሉበታል።
2 ዮሐንስ 1:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከልጆችሽ አንዳንዶቹ ከአብ በተሰጠን ትእዛዝ መሠረት በእውነት ጸንተው እየኖሩ በማግኘቴ እጅግ ደስ ብሎኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከልጆችሽ አንዳንዶቹ ከአባት እንደተቀበልነው ትእዛዝ መሠረት በእውነት የሚመላለሱ ሆነው በማግኘቴ እጅግ ደስ ብሎኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከልጆችሽ አንዳንዶቹ አብ ባዘዘን መሠረት በእውነት ጸንተው በማግኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትእዛዝን ከአብ እንደ ተቀበልን ከልጆችሽ በእውነት የሚሄዱ አንዳንዶችን ስለ አገኘኋቸው እጅግ ደስ ብሎኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትእዛዝን ከአብ እንደ ተቀበልን ከልጆችሽ በእውነት የሚሄዱ አንዳንዶችን ስለ አገኘኋቸው እጅግ ደስ ብሎኛል። |
ጥበበኛ የሆነ እነዚህን ነገሮች ያስተውላል፤ አስተዋይም እነዚህን ነገሮች ይረዳል። የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ነውና፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ዐመፀኞች ግን ይሰናከሉበታል።
እውነተኛ ትምህርት በአፉ ነበር፤ ምንም ዐይነት የሐሰት ነገር በአንደበቱ አልተገኘም፤ ከእኔ ጋራ በሰላምና በቅንነት ተራመደ፤ ብዙዎችንም ከኀጢአት መለሰ።
ተግባራቸው እንደ ወንጌል እውነት አለመሆኑን በተረዳሁ ጊዜ፣ በሁሉም ፊት ኬፋን እንዲህ አልሁት፤ “አንተ አይሁዳዊ ነህ፤ ሆኖም በአሕዛብ ሥርዐት እንጂ በአይሁድ ሥርዐት አትኖርም፤ ታዲያ አሕዛብ የአይሁድን ሥርዐት እንዲከተሉ እንዴት ታስገድዳቸዋለህ?
ክርስቶስ እንደ ወደደን ራሱንም ስለ እኛ መልካም መዐዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር እንደ ሰጠ እናንተም በፍቅር ተመላለሱ።
ከብዙ ጊዜ በኋላ እንደ አዲስ ስለ እኔ ማሰብ በመጀመራችሁ፣ በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፤ በርግጥ በተግባር ለመግለጽ ዕድሉ አልነበራችሁም እንጂ ማሰቡንስ ታስቡልኝ ነበር።