1 ሳሙኤል 6:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወርቅ ዐይጦቹም ቍጥር፣ ዐምስቱ የፍልስጥኤም ገዦች በሚያስተዳድሯቸው የተመሸጉ ከተሞችና ከእነዚህ ውጭ ባሉት መንደሮቻቸው ቍጥር ልክ ነው። በቤትሳሚሳዊው በኢያሱ ዕርሻ ውስጥ የእግዚአብሔርን ታቦት ያስቀመጡበት ያ ትልቅ ድንጋይ እስከ ዛሬ ምስክር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወርቅ ዐይጦቹም ቍጥር፥ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎች በሚያስተዳድሯቸው የተመሸጉ ከተሞችና ከእነዚህ ውጭ ባሉት መንደሮቻቸው ቍጥር ልክ ነው። በቤትሼሜሻዊው በኢያሱ እርሻ ውስጥ የጌታን ታቦት ያስቀመጡበት ያ ትልቅ ቋጥኝ እስከ ዛሬ ምስክር ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ከተላኩት መካከል በተመሸጉ ከተሞችና ቅጽር ባልተሠራላቸው መንደሮች ሆነው አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎች በሚያስተዳድሩት በእያንዳንዱ ከተማ ስም በአይጥ አምሳል የተሠሩ አምስት የወርቅ እንክብሎች ነበሩ። በቤትሼሜሽ በሚኖረው በኢያሱ እርሻ ውስጥ የእግዚአብሔርን ታቦት ያኖሩበትም ታላቅ ቋጥኝ እስከ ዛሬ ድረስ ምስክር ሆኖ ይታያል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወርቁም አይጦች ቍጥር ለአምስቱ የፍልስጥኤማውያን አለቆች እንደ ነበሩት ከተሞች ሁሉ ቍጥር እንዲሁ ነበረ፤ እነርሱም እስከ ታላቁ ድንጋይ የሚደርሱ ቅጥር ያላቸው ከተሞችና የፌርዜዎን መንደሮች ናቸው። በዚህም ድንጋይ ላይ የእግዚአብሔርን ታቦት አስቀመጡ፤ ድንጋዩም እስከ ዛሬ ድረስ በቤትሳሚሳዊው በኦሴዕ እርሻ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዲቱ ለአቃሮን የወርቁም አይጦች ቁጥር ለአምስቱ የፍልስጥኤማውያን አለቆች እንደ ነበሩት ከተሞች ሁሉ ቁጥር እንዲሁ ነበረ፥ እነርሱም እስከ ታላቁ ድንጋይ የሚደርሱ ከተሞችና መንደሮች ናቸው። በዚህም ድንጋይ ላይ የእግዚአብሔርን ታቦት አስቀመጡ፥ ድንጋዩም እስከ ዛሬ ድረስ በቤትሳሚሳዊው በኢያሱ እርሻ አለ። |
ከግብጽ በስተምሥራቅ ከሚገኘው ከሺሖር ወንዝ አንሥቶ፣ በሰሜን እስከ አቃሮን ወሰን ያለው አገር፣ ሁሉም እንደ ከነዓናውያን ምድር ይቈጠራል። ይኸውም በጋዛ፣ በአሽዶድ፣ በአስቀሎና፣ በጋትና በአቃሮን የሚኖሩትን የዐምስቱን የፍልስጥኤማውያን ገዦች ምድር የሚያካትት ሲሆን፣ ይህም የኤዋውያን ምድር ነበር።
ፍልስጥኤማውያንም፣ “የምንልከው የበደል መሥዋዕት ምን መሆን አለበት?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “እናንተንም ሆነ አለቆቻችሁን የመታው መቅሠፍት አንድ ዐይነት በመሆኑ፣ በፍልስጥኤማውያን ገዦች ቍጥር ልክ ዐምስት የወርቅ ዕባጮችና ዐምስት የወርቅ ዐይጦች ላኩ።