ይሥሐቅ አርጅቶ፣ ዐይኖቹ ደክመው ማየት በተሳናቸው ጊዜ፣ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፣ “ልጄ ሆይ” አለው። እርሱም፣ “እነሆ፤ አለሁ” አለ።
1 ሳሙኤል 4:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዔሊ የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ስለ ነበር ዐይኖቹ ደክመው ማየት ተስኗቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔሊ የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ስለ ነበር ዐይኖቹ ደክመው ማየት ተስኗቸው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ዘመን ዔሊ የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ነበር፤ ዐይኑም ፈዞ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሊም የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ነበረ፤ ዐይኖቹም ፈዝዘው አያይም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሊም የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ነበረ፥ ዓይኖቹም ማየት እስኪሳናቸው ድረስ ፈዝዘው ነበር። |
ይሥሐቅ አርጅቶ፣ ዐይኖቹ ደክመው ማየት በተሳናቸው ጊዜ፣ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፣ “ልጄ ሆይ” አለው። እርሱም፣ “እነሆ፤ አለሁ” አለ።
ስለዚህ የኢዮርብዓም ሚስት ያላትን አድርጋ በሴሎ ወደሚገኘው ወደ አኪያ ቤት ሄደች። በዚህ ጊዜ አኪያ ከማርጀቱ የተነሣ ዐይኖቹ ፈዝዘው ነበር።
የዕድሜያችን ዘመን ሰባ ዓመት፣ ቢበዛም ሰማንያ ነው፤ ከዚያ በላይ ከሆነም ድካምና መከራ ብቻ ነው፤ ቶሎ ያልፋልና፤ እኛም ወዲያው እንነጕዳለን።