1 ሳሙኤል 26:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመቀጠልም፣ “ጌታዬ አገልጋዩን የሚያሳድደው ስለ ምንድን ነው? ምን አደረግሁ? ምን በደልስ ፈጸምሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመቀጠልም፥ “ጌታዬ አገልጋዩን የሚያሳድደው ስለ ምንድነው? ምን አደረግሁ? ምን በደልስ ፈጸምሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ አንተ ጌታዬ እኔን አገልጋይህን ስለምን ታሳድደኛለህ? ያደረግኹት ነገር ምንድን ነው? ምንስ ወንጀል ፈጸምኩ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም አለ፥ “ጌታዬ አገልጋዩን ስለምን ያሳድዳል? ምን አደረግሁ? ምንስ ክፋት በእጄ ላይ ተገኘብኝ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ አለ፦ ጌታዬ ባሪያውን ስለ ምን ያሳድዳል? ምን አደረግሁ? ምንስ ክፋት በእጄ ላይ ተገኘብኝ? |
ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ፣ ከራሴ ጠጕር በዙ፤ ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልጉ፣ በከንቱም የሚጠሉኝ ብዙዎች ሆኑ፤ ያልሰረቅሁትን ነገር፣ መልሰህ አምጣ ተባልሁ።
ኤርምያስም ንጉሡ ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፤ “በግዞት ቤት ያሰራችሁኝ በአንተና በመኳንንትህ ወይም በዚህ ሕዝብ ላይ ምን ወንጀል ፈጽሜ ነው?
ከዚህ በኋላ ዳዊት በአርማቴም ካለችው ከነዋት ዘራማ ሸሽቶ ወደ ዮናታን በመሄድ፣ “ምን አድርጌአለሁ? ምን በደልስ ፈጸምሁ? አባትህ ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልገውስ በፊቱ ምን ተገኝቶብኝ ነው?” ሲል ጠየቀው።