ይሁዳም ዕቃዎቹን ዐውቆ፣ “ልጄ ሴሎም እንዲያገባት ባለማድረጌ፣ እርሷ ከእኔ ይልቅ ትክክል ናት” አለ። ከዚያም በኋላ ከርሷ ጋራ አልተኛም።
1 ሳሙኤል 24:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያደረግህልኝን በጎ ነገር ይኸው ነግረኸኛል፤ እግዚአብሔር እኔን በእጅህ ጥሎኝ ነበር፤ አንተ ግን አልገደልኸኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አለ፤ “ክፉ ሳደርግብህ፥ በጎ መልሰህልኛልና፥ አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በእጅህ ቢጥለኝም እንኳ አንተ አልገደልከኝምና ለእኔ በጎ አድራጊ መሆንህንም ዛሬ አስመስክረሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ዳዊትን አለው፥ “እኔ ክፉ በመለስሁልህ ፋንታ በጎ መልሰህልኛልና አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶኝ ሳለ አልገደልኸኝምና ለእኔ መልካም እንዳደረግህልኝ አንተ ዛሬ አሳየኸኝ። |
ይሁዳም ዕቃዎቹን ዐውቆ፣ “ልጄ ሴሎም እንዲያገባት ባለማድረጌ፣ እርሷ ከእኔ ይልቅ ትክክል ናት” አለ። ከዚያም በኋላ ከርሷ ጋራ አልተኛም።
ዳዊትም እንደ ገና፣ “የቅዒላ ገዦች እኔንና ሰዎቼን ለሳኦል አሳልፈው ይሰጡናል?” ሲል ጠየቀ። እግዚአብሔርም፣ “አዎን አሳልፈው ይሰጧችኋል” አለው።
ሳኦል የዳዊትን ወደ ቅዒላ መሄድ በሰማ ጊዜ፣ “ዳዊት መዝጊያና የብረት መወርወሪያ ወዳላት ከተማ መግባቱ፣ ራሱን በራሱ እንደ ማሰር ስለ ሆነ፣ ይህን ሰው እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኛል” አለ።
በዛሬው ዕለት በዋሻው ውስጥ እግዚአብሔር አንተን እንዴት አድርጎ በእጄ ላይ እንደ ጣለህ እነሆ፤ በገዛ ዐይንህ አይተሃል፤ አንዳንዶች እንድገድልህ ገፋፍተውኝ ነበር፤ እኔ ግን፣ ‘እግዚአብሔር በቀባው በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም’ በማለት ራራሁልህ።
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ጽድቁና እንደ ታማኝነቱ ይክፈለው። እኔ ግን ዛሬ እግዚአብሔር አንተን በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኝ ሳለ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን አላነሣሁም።
አቢሳም ዳዊትን፣ “ዛሬ እግዚአብሔር ጠላትህን በእጅህ ላይ ጥሎታል፤ አሁንም እኔ አንድ ጊዜ በጦር ወግቼ ከመሬት ጋራ ላጣብቀው፤ መድገምም አያስፈልገኝም” አለው።