ወዲያውኑም ብረቱ፣ ሸክላው፣ ናሱ፣ ብሩና ወርቁ ተሰባበሩ፤ በበጋ ወራት በዐውድማ ላይ እንደሚገኝ እብቅም ሆኑ፤ ነፋስም አንዳች ሳያስቀር ጠራረጋቸው፤ ምስሉን የመታው ድንጋይ ግን ታላቅ ተራራ ሆነ፤ ምድርንም ሞላ።
1 ሳሙኤል 23:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ “እነሆ፤ ፍልስጥኤማውያን በቅዒላ ላይ ጦርነት ከፍተው፣ ዐውድማውን እየዘረፉት ነው” ብለው ለዳዊት ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ “እነሆ፤ ፍልስጥኤማውያን በቅዒላ ላይ ጦርነት ከፍተው፥ ዐውድማውን እየዘረፉት ነው” ብለው ለዳዊት ነገሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያን በቀዒላ ከተማ ላይ አደጋ መጣላቸውንና በቅርቡ የተሰበሰበውንም የአዲሱን መከር እህል ዘርፈው መውሰዳቸውን ዳዊት ሰማ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዳዊትም፥ “እነሆ፥ ፍልስጥኤማውያን ቂአላን ይወጋሉ፤ አውድማውንም ይዘርፋሉ” ብለው ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዳዊትም፦ እነሆ፥ ፍልስጥኤማውያን ቅዒላን ይወጋሉ፥ አውድማውንም ይዘርፋሉ የሚል ወሬ ደረሰው። |
ወዲያውኑም ብረቱ፣ ሸክላው፣ ናሱ፣ ብሩና ወርቁ ተሰባበሩ፤ በበጋ ወራት በዐውድማ ላይ እንደሚገኝ እብቅም ሆኑ፤ ነፋስም አንዳች ሳያስቀር ጠራረጋቸው፤ ምስሉን የመታው ድንጋይ ግን ታላቅ ተራራ ሆነ፤ ምድርንም ሞላ።
እኔም ይህን አደርግባችኋለሁ፤ ድንገተኛ ድንጋጤ፣ የሚቀሥፍ በሽታ፣ ዐይናችሁን የሚያጠፋና ሰውነታችሁን የሚያመነምን ትኵሳት አመጣባችኋለሁ፤ እህል የምትዘሩት በከንቱ ነው፤ ጠላቶቻችሁ ይበሉታልና።
ትዘራለህ፤ ነገር ግን አታጭድም፤ የወይራ ዘይት ትጨምቃለህ፤ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፤ ወይንን ትቈርጣለህ፤ ነገር ግን የወይን ጠጅ አትጠጣም።
እስክትጠፋም ድረስ የእንስሳትህን ግልገልና የምድርህን ሰብል ይበላል፤ እስኪያጠፋህም ድረስ እህል፣ አዲስ የወይን ጠጅ ሆነ ዘይት፣ የመንጋህን ጥጃ ሆነ የበግና የፍየል መንጋህን ግልገል አያስቀርልህም።
የእግዚአብሔር መልአክ ዖፍራ ወደምትባል መንደር መጥቶ፣ በአቢዔዝራዊው በኢዮአስ ዕርሻ ውስጥ በሚገኝ በአንድ የባሉጥ ዛፍ ሥር ተቀመጠ፤ የኢዮአስም ልጅ ጌዴዎን፣ ምድያማውያን እንዳያዩበት ደብቆ በወይን መጭመቂያው ስፍራ ስንዴውን ይወቃ ነበር።
እነርሱም በምድሪቱ ላይ ሰፍረው እስከ ጋዛ ያለውን ሰብል በማጥፋት አንዳችም የእህል ዘር ለእስራኤል አያስተርፉም፣ የበግም ሆነ የከብት ወይም የአህያ መንጋ አይተዉም ነበር።