La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 22:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን እዚያ ከነበሩት የሳኦል ሹማምት ጋራ ቆሞ የነበረው ኤዶማዊው ዶይቅ እንዲህ አለ፣ “የእሴይ ልጅ በኖብ ወዳለው ወደ አኪጦብ ልጅ ወደ አቢሜሌክ ሲመጣ አይቻለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን እዚያ ከነበሩት የሳኦል አገልጋዮች ጋር ቆሞ የነበረው ኤዶማዊው ዶይቅ እንዲህ አለ፥ “የእሴይ ልጅ በኖብ ወዳለው ወደ አኪጦብ ልጅ ወደ አቢሜሌክ ሲመጣ አይቻለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህን ጊዜ ከባለሥልጣኖቹ ጋር ኤዶማዊው ዶይቅ እዚያ ቆሞ ስለ ነበር “እኔ የእሴይን ልጅ በኖብ ወደሚገኘው የአሒጡብ ልጅ ወደ ሆነው ወደ አቤሜሌክ በመጣ ጊዜ አይቼዋለሁ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሳ​ኦ​ልም በቅ​ሎ​ዎች ጠባቂ ሶር​ያ​ዊው ዶይቅ መልሶ፥ “የእ​ሴይ ልጅ ወደ ኖብ ወደ አኪ​ጦብ ልጅ ወደ ካህኑ አቤ​ሜ​ሌክ ሲመጣ አይቼ​ዋ​ለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሳኦልም ባሪያዎች አጠገብ የቆመው ኤዶማዊው ዶይቅ መልሶ፦ የእሴይ ልጅ ወደ ኖብ ወደ አኪጦብ ልጅ ወደ አቢሜሌክ ሲመጣ አይቼዋለሁ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 22:9
8 Referencias Cruzadas  

ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አያመልጥም፤ ውሸት የሚነዛም ሳይቀጣ አይቀርም።


ገዥ የሐሰት ወሬ የሚሰማ ከሆነ፣ ሹማምቱ ሁሉ ክፉዎች ይሆናሉ።


በዚህ ቀን ኖብ ይደርሳሉ፤ እጃቸውን በኢየሩሳሌም ኰረብታ፣ በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ላይ በዛቻ ነቀነቁ።


ደምን ለማፍሰስ ወሬ የሚያቀብሉ በውስጥሽ አሉ፤ በኰረብታ ቤተ ጣዖት የተሠዋውን የሚበሉና ዝሙትን የሚፈጽሙ ሰዎች በመካከልሽ ይገኛሉ።


ኤፉድ ይለብስ የነበረውም አኪያ በመካከላቸው ነበር። እርሱም በሴሎ የእግዚአብሔር ካህን የነበረው የዔሊ ልጅ፣ የፊንሐስ ልጅ የኢካቦድ ወንድም የአኪጦብ ልጅ ነበር። ዮናታን አለመኖሩን ግን ያወቀ ሰው አልነበረም።