ዳዊትም፣ “አትፍራ፤ ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ስል በርግጥ ቸርነት አደርግልሃለሁና። የአባትህን የሳኦልን ምድር በሙሉ እመልስልሃለሁ፤ ዘወትርም ከማዕዴ ትበላለህ” አለው።
1 ሳሙኤል 22:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም ከእኔ ጋራ ቈይ፤ አትፍራ፤ የአንተን ሕይወት የሚፈልግ የእኔን ሕይወት የሚፈልግ ነውና። ዐብረኸኝ በሰላም ትኖራለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም ከእኔ ጋር ቆይ፤ አትፍራ፤ የአንተን ሕይወት የሚፈልግ የእኔን ሕይወት ይፈልጋል። አብረኸኝ በሰላም ትኖራለህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ግን ከእኔ ጋር ኑር፤ አይዞህ አትፍራ፤ በእርግጥ ሳኦል አንተንም እኔንም ለመግደል ይፈልጋል፤ ነገር ግን አንተ ከእኔ ጋር በሰላም ትኖራለህ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ወዲህ ከእኔ ጋር ተቀመጥ፤ አትፍራ፤ ለእኔ ነፍስ የደኅንነት ቦታን እንደምፈልግ ለአንተም ነፍስ የደኅንነት ቦታን እፈልጋለሁና፥ ከእኔም ጋር ተጠብቀህ ትኖራለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍሴን የሚፈልግ የአንተን ነፍስ ይፈልጋልና፥ ከእኔም ጋር ተጠብቀህ ትኖራለህና በእኔ ዘንድ ተቀመጥ፥ አትፍራ አለው። |
ዳዊትም፣ “አትፍራ፤ ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ስል በርግጥ ቸርነት አደርግልሃለሁና። የአባትህን የሳኦልን ምድር በሙሉ እመልስልሃለሁ፤ ዘወትርም ከማዕዴ ትበላለህ” አለው።
ንጉሡም ካህኑን አብያታርን፣ “ሞት የሚገባህ ሰው ነበርህ፤ ነገር ግን የጌታ እግዚአብሔርን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ስለ ተሸከምህ፣ አባቴ የተቀበለውንም መከራ ሁሉ ዐብረኸው ስለ ተቀበልህ፣ እኔ አሁን አልገድልህም፤ ዓናቶት ወዳለው ዕርሻህ ሂድ” አለው።
‘ባሪያ ከጌታው አይበልጥም’ ብዬ የነገርኋችሁን ቃል አስታውሱ። እኔን አሳድደውኝ ከሆነ፣ እናንተንም ያሳድዷችኋል፤ ቃሌን ጠብቀው ከሆነም ቃላችሁን ይጠብቃሉ።
እኔ ከእነርሱ ጋራ ሳለሁ፣ በሰጠኸኝ ስም ከለልኋቸው፤ ጠበቅኋቸውም፤ የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ከአንዱ ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ ማንም አልጠፋም።
እርሱም፣ “አትፍራ፤ አባቴ ሳኦል እጁን በአንተ ላይ አያሳርፍም፤ በእስራኤል ላይ ትነግሣለህ፤ እኔም ካንተ ቀጥዬ ሁለተኛ ሰው እሆናለሁ፤ ይህንም አባቴ ሳኦል እንኳ ያውቀዋል” አለው።