ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት እያስገደለች በነበረበት ጊዜ፣ አብድዩ መቶውን ነቢያት ወስዶ ዐምሳ ዐምሳውን በሁለት ዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውሃ ይሰጣቸው ነበር።
1 ሳሙኤል 22:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ ግን፣ “አቢሜሌክ ሆይ፤ አንተም የአባትህም ቤተ ሰብ በሙሉ በርግጥ ትሞታላችሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡ ግን፥ “አቢሜሌክ ሆይ፤ አንተም የአባትህም ቤተሰብ በሙሉ በእርግጥ ትሞታላችሁ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም “አቤሜሌክ ሆይ! አንተና መላው ዘመዶችህ ሞት ይገባችኋል!” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም፥ “አቤሜሌክ ሆይ! አንተና የአባትህ ቤት ሁሉ ፈጽማችሁ ትሞታላችሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም፦ አቢሜሌክ ሆይ፥ አንተና የአባትህ ቤት ሁሉ ፈጽማችሁ ትሞታላችሁ አለ። |
ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት እያስገደለች በነበረበት ጊዜ፣ አብድዩ መቶውን ነቢያት ወስዶ ዐምሳ ዐምሳውን በሁለት ዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውሃ ይሰጣቸው ነበር።
ስለዚህም እርሷ፣ “ነገ በዚህ ሰዓት ያንተንም ነፍስ ከእነዚያ እንደ አንዱ ነፍስ ሳላደርጋት ብቀር አማልክት እንዲህ ያድርጉብኝ፤ ከዚህ የባሰም ያምጡብኝ” ስትል ወደ ኤልያስ መልእክተኛ ላከች።
ይልቁንም መርዶክዮስ ከእነማን ወገን መሆኑን በተረዳ ጊዜ፣ መርዶክዮስን ብቻ መግደል እንደ ኢምንት ቈጠረው፤ ስለዚህ ሐማ በመላው የጠረክሲስ መንግሥት ውስጥ የሚገኙትንና የመርዶክዮስ ወገን የሆኑትን አይሁድ ሁሉ ለማጥፋት ዘዴ ፈለገ።
ንጉሡም ለኮከብ ቈጣሪዎቹ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ሕልሙንና ትርጕሙን ባትነግሩኝ አካላችሁ እንዲቈራረጥና ቤቶቻችሁም የፍርስራሽ ክምር እንዲሆኑ ወስኛለሁ፤
ሄሮድስ ጠቢባኑ እንዳታለሉት በተረዳ ጊዜ በጣም ተናደደ። ከጠቢባኑ በተነገረው መሠረት፣ ዕድሜያቸው ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የሆኑትን የቤተ ልሔምንና የአካባቢዋን መንደሮች ወንድ ልጆች ሁሉ ልኮ አስገደለ።
ሄሮድስም ጴጥሮስን አስፈልጎ ባጣው ጊዜ፣ ዘብ ጠባቂዎቹን በጥብቅ ከመረመረ በኋላ እንዲገደሉ አዘዘ። ከዚያም ሄሮድስ ከይሁዳ ወደ ቂሳርያ ወርዶ እዚያ ተቀመጠ።
ስለ እርሱ እግዚአብሔርን ስጠይቅስ ያ ቀን የመጀመሪያ ጊዜዬ ነበርን? ፈጽሞ አልነበረም፤ ይህን ጕዳይ በተመለከተ አገልጋይህ የሚያውቀው ምንም ነገር ስለሌለ ንጉሥ እኔን አገልጋዩን ወይም ከአባቴ ቤተ ሰብ ማንንም ጥፋተኛ አያድርግ።”
ከዚያም ንጉሡ በአጠገቡ የቆሙትን ዘቦች፣ “እነዚህም የእግዚአብሔር ካህናት ከዳዊት ጋራ ስላበሩ፣ ዳዊት መኰብለሉንም እያወቁ ስላልነገሩኝ ዙሩና ግደሏቸው” ሲል አዘዛቸው። የንጉሡ ሹማምት ግን እጃቸውን አንሥተው የእግዚአብሔርን ካህናት ለመምታት ፈቃደኞች አልሆኑም።