1 ሳሙኤል 20:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ‘መልካም ነው’ ካለ፣ አገልጋይህን የሚያሠጋው የለም፤ ከተቈጣ ግን፣ ክፉ ነገር እንዳሰበብኝ ታረጋግጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ‘መልካም ነው’ ካለ፥ አገልጋይህን የሚያሰጋው የለም፤ ከተቆጣ ግን፥ ክፉ ነገር እንዳሰበብኝ ታረጋግጣለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም ‘እሺ’ ቢል፥ እኔ አገልጋይህ በሰላም እንደምኖር ዐውቃለሁ፤ ንጉሡ ከተቈጣ ግን ጒዳት ሊያደርስብኝ የወሰነ መሆኑን ታውቃለህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፦ መልካም ነው ቢል ለእኔ ለባሪያህ ሰላም ይሆናል፤ ቢቈጣ ግን ክፋት ከእርሱ ዘንድ በእኔ ላይ እንደ ተቈረጠች ዕወቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ መልካም ነው ቢል ለእኔ ለባሪያህ ደኅንነት ይሆናል፥ ቢቆጣ ግን ክፋት ከእርሱ ዘንድ በእኔ ላይ እንደ ተቆረጠች እወቅ። |
ንጉሡ ከተቀመጠበት በቍጣ ተነሣ፤ የወይን ጠጁንም ትቶ ወደ ቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ ሄደ። ሐማ ግን ንጉሡ ሊያጠፋው ቈርጦ መነሣቱን ስላወቀ፣ ንግሥት አስቴር ሕይወቱን እንድታተርፍለት ለመማጠን በዚያው ቀረ።
አሁንም በጌታችንና በመላው ቤተ ሰቡ ላይ መከራ እያንዣበበ ስለ ሆነ፣ አስቢበትና የምታደርጊውን አድርጊ፤ እርሱ እንደ ሆነ እንዲህ ያለ ምናምንቴ ሰው ስለ ሆነ፣ ደፍሮ የሚነግረው አንድም ሰው የለም።”