1 ሳሙኤል 20:41 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጁ ከሄደ በኋላ፣ ዳዊት ከድንጋዩ በስተ ደቡብ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ በዮናታን ፊት ሦስት ጊዜ በምድር ላይ ተደፍቶ ሰገደለት፤ ከዚያም ተሳሳሙ፤ ተላቀሱም፤ በይበልጥ ያለቀሰው ግን ዳዊት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጁ ከሄደ በኋላ፥ ዳዊት ከድንጋዩ በስተ ደቡብ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ በዮናታን ፊት ሦስት ጊዜ በምድር ላይ ተደፍቶ ሰገደለት፤ ከዚያም ተሳሳሙ፤ ተላቀሱም፤ በይበልጥ ያለቀሰው ግን ዳዊት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጁም ከሄደ በኋላ ዳዊት ከድንጋዩ ቊልል በስተኋላ ከተደበቀበት ስፍራ ወጥቶ በጒልበቱ በመንበርከክ ሦስት ጊዜ ወደ መሬት ሰገደ፤ እርሱና ዮናታን በሚሳሳሙበት ጊዜ ሁለቱም ያለቅሱ ነበር፤ ከዮናታንም ይልቅ የዳዊት ሐዘን የበረታ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናውም በሄደ ጊዜ ዳዊት ከኤርገብ ተነሣ፤ በምድርም ላይ በግንባሩ ተደፋ፤ ሦስት ጊዜም ሰገደ፤ እርስ በእርሳቸውም ተሳሳሙ፤ ለረዥም ሰዓትም ተላቀሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብላቴናውም በሄደ ጊዜ ዳዊት ከስፍራው በደቡብ አጠገብ ተነሣ፥ በምድርም ላይ በግምባሩ ተደፋ፥ ሦስት ጊዜም ለሰላምታ ሰገደ፥ እየተላቀሱም እርስ በእርሳቸው ተሳሳሙ፥ ይልቁንም ዳዊት እጅግ አለቀስ። |
ላባም የእኅቱ ልጅ ያዕቆብ መምጣቱን እንደ ሰማ ሊቀበለው ፈጥኖ ወጣ። ዐቅፎ ከሳመውም በኋላ፣ ወደ ቤቱ ይዞት ሄደ። ያዕቆብም ሁኔታውን ሁሉ ለላባ ነገረው።
በዚህ ጊዜ ዮሴፍ የምድሪቱ ገዥ ነበር፤ ለአገሩ ሰዎች ሁሉ እህል የሚሸጥላቸው እርሱ ነበር። የዮሴፍ ወንድሞችም እንደ ደረሱ፣ ከፊቱ ቀርበው ወደ ምድር ለጥ ብለው እጅ ነሡት።
በሦስተኛውም ቀን የተቀደደ ልብስ የለበሰ፣ በራሱም ላይ ትቢያ የነሰነሰ አንድ ሰው ከሳኦል ሰፈር መጣ። ወደ ዳዊት እንደ ደረሰም፣ ወደ መሬት ለጥ ብሎ በአክብሮት እጅ ነሣ።
ወንድሜ ዮናታን ሆይ፤ እኔ ስለ አንተ ዐዘንሁ፤ አንተ ለእኔ እጅግ ውድ ነበርህ፤ ፍቅርህ ለእኔ ድንቅ ነበረ፤ ከሴት ፍቅርም ይልቅ ግሩም ነበር።
የቴቁሔዪቱም ሴት ወደ ንጉሡ ገብታ፣ በንጉሡ ፊት ወደ መሬት በግምባሯ ተደፍታ እጅ በመንሣት አክብሮቷን ከገለጠች በኋላ፣ “ንጉሥ ሆይ! እርዳኝ” አለች።
የሳኦል ልጅ፣ የዮናታን ልጅ ሜምፊቦስቴ ወደ ዳዊት በመጣ ጊዜ፣ አክብሮቱን ለመግለጥ ለጥ ብሎ እጅ ነሣ። ዳዊትም፣ “ሜምፊቦስቴ” ብሎ ጠራው። እርሱም፣ “እነሆ፤ አገልጋይህ” አለ።
ከዚያም ሳሙኤል የዘይቱን ብርሌ ወስዶ፣ ዘይቱን በሳኦል ራስ ላይ ካፈሰሰ በኋላ እንዲህ ሲል ሳመው፤ “በርስቱ ላይ ገዥ ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶህ የለምን?