1 ሳሙኤል 20:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከነገ ወዲያ ምሽት ላይ ይህ ችግር በተፈጠረ ዕለት ወደ ተደበቅህበት ስፍራ ሂድና ኤዜል በተባለው ድንጋይ አጠገብ ቈይ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከነገ ወዲያ ምሽት ላይ ይህ ችግር በተፈጠረ ዕለት ወደ ተደበቅህበት ስፍራ ሂድና ኤጼል በተባለው ድንጋይ አጠገብ ቆይ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከነገ ወዲያ ወደ ማታ ጊዜ ከዚህ በፊት ይህ ችግር ሲጀመር ወደ ተደበቅህበት ቦታ ሄደህ ከኤጼል ድንጋይ በስተጀርባ ተሸሸግ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሦስት ቀንም ያህል ቈይ፤ ከዚህም በኋላ በፈለገህ ጊዜ ትመጣና ነገሩ በተደረገበት ቀን በተሸሸግህበት ስፍራ ትቀመጣለህ፤ በኤርገብ ድንጋይም አጠገብ ቈይ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሦስት ቀንም ያህል ቆይ፥ ከዚህም በኋላ ፈጥነህ ውረድ፥ ነገሩም በተደረገበት ቀን ወደ ተሸሸግህበት ስፍራ ሂድ፥ በኤዜል ድንጋይም አጠገብ ቆይ። |
እንዲህ ሲል አስጠነቀቀው፤ “አባቴ ሳኦል ሊገድልህ አጋጣሚ እየፈለገ ነው፤ ነገ ጧት ተጠንቀቅ፤ ወደ አንድ መደበቂያ ቦታም ሂድ፤ በዚያም ቈይ።
ስለዚህ ዳዊት እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ነገ የወር መባቻ በዓል ስለ ሆነ፣ ከንጉሡ ጋራ ምሳ መብላት ይጠበቅብኛል፤ ነገር ግን እስከ ከነገ ወዲያ ማታ ድረስ ከዱር ልደበቅ፤