እግዚአብሔር በጠላቶቻቸው ላይ እንዲደሰቱ ስላደረጋቸው፣ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሁሉ በኢዮሣፍጥ እየተመሩ፣ በታላቅ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
1 ሳሙኤል 2:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፤ “ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፤ ቀንዴም በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህ ደስ ይለኛልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፦ “ልቤ በጌታ ደስ ይለዋል፥ ቀንዴም በጌታ ከፍ ከፍ ብሏል፤ በማዳንህ ደስ ብሎኛልና፥ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፦ “ልቤ በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፤ ክብሬም በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ ብሎአል፤ በማዳንህ ስለ ተደሰትኩ፤ በጠላቶቼ ላይ እሳለቃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐናም ጸለየች፤ እንዲህም አለች፦ “ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፤ ቀንዴም በአምላኬ በመድኀኒቴ ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህም ደስ ብሎኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐናም ስትጸልይ እንዲህ አለች፦ ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፥ ቀንዴ በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፥ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፥ በማዳንህ ደስ ብሎኛል። |
እግዚአብሔር በጠላቶቻቸው ላይ እንዲደሰቱ ስላደረጋቸው፣ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሁሉ በኢዮሣፍጥ እየተመሩ፣ በታላቅ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
በምስጋናና በጸሎት ጊዜ ይመራ የነበረው የዋናው አለቃ የአሳፍ ልጅ፣ የዘብዲ ልጅ፣ የሚካ ልጅ መታንያ፣ ከወንድሞቹ ሁለተኛ የሆነው በቅቡቅያ፣ የኤዶታም ልጅ፣ የጋላል ልጅ፣ የሳሙስ ልጅ አብድያ።
ከዚያም ሙሴና እስራኤላውያን ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፤ “ከፍ ከፍ ብሎ ከብሯልና፣ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን፣ በባሕር ውስጥ ጥሏልና።
በግርማው እንደ በኵር ኰርማ ነው፤ ቀንዶቹም የጐሽ ቀንዶች ናቸው። በእነርሱም ሕዝቦችን፣ በምድር ዳርቻ ላይ ያሉትን እንኳ ሳይቀር ይወጋል፤ እነርሱም የኤፍሬም ዐሥር ሺሕዎቹ ናቸው፤ የምናሴም ሺሕዎቹ እንደዚሁ ናቸው።”
“ሰማይ ሆይ፤ በርሷ ላይ ሐሤት አድርግ! ቅዱሳን፣ ሐዋርያትና ነቢያትም ሐሤት አድርጉ! በእናንተ ላይ ባደረሰችው ነገር እግዚአብሔር ፈርዶባታልና።”
ይህም በየዓመቱ ይደጋገም ነበር፤ ሐና ወደ እግዚአብሔር ቤት በምትወጣበት ጊዜ ሁሉ፣ እስክታለቅስና መብላት እስኪያቅታት ድረስ ጣውንቷ ታበሳጫት ነበር።