በተራራ ዐናት ላይ እንደ ተተከለ ሰንደቅ ዐላማ፣ በኰረብታም ላይ እንደ ቆመ ምልክት ሆናችሁ እስክትቀሩ ድረስ በአንድ ሰው ዛቻ፣ ሺሕ ሰው ይሸሻል፤ በዐምስት ሰው፣ ሁላችሁ ትሸሻላችሁ።”
1 ሳሙኤል 17:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያንም ሰውየውን ባዩት ጊዜ ሁሉም በታላቅ ፍርሀት ከፊቱ ሸሹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያንም ሰውየውን ባዩት ጊዜ ሁሉም በታላቅ ፍርሃት ከፊቱ ሸሹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያንም ጎልያድን ባዩ ጊዜ በታላቅ ፍርሀት ሸሹ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ሰውዬውን ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተው ከፊቱ ሸሹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ሰውዮውን ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተው ከእርሱ ሸሹ። |
በተራራ ዐናት ላይ እንደ ተተከለ ሰንደቅ ዐላማ፣ በኰረብታም ላይ እንደ ቆመ ምልክት ሆናችሁ እስክትቀሩ ድረስ በአንድ ሰው ዛቻ፣ ሺሕ ሰው ይሸሻል፤ በዐምስት ሰው፣ ሁላችሁ ትሸሻላችሁ።”
ለዳዊት ቤት፣ “ሶርያና ኤፍሬም ተባብረዋል” የሚል ወሬ በደረሰ ጊዜ፣ የዱር ዛፍ በነፋስ እንደሚናወጥ የአካዝና የሕዝቡ ልብ እንዲሁ ተናወጠ።
“ ‘ከእናንተ በሕይወት የተረፉትን፣ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ ድንጋጤ እሰድድባቸዋለሁ፤ ነፋስ የሚያንቀሳቅሰው የቅጠል ድምፅ ያስበረግጋቸዋል፤ የሚያሳድዳቸውም ሳይኖር ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሮጣሉ፤ ይወድቃሉም።
ኔፊሊምንም በዚያ አይተናል፤ የዔናቅ ዝርያዎች የመጡት ከኔፊሊም ነው። ራሳችንን ስናየው እንደ አንበጣ ነበርን፤ በእነርሱ ዐይን የታየነውም በዚሁ መልክ ነበር።”
መጠጊያ ዐለታቸው ካልሸጣቸው፣ እግዚአብሔር ካልተዋቸው በቀር፣ አንድ ሰው እንዴት ሺሑን ያሳድዳል? ሁለቱስ እንዴት ዐሥር ሺሑን እንዲሸሹ ያደርጋሉ?
እስራኤላውያንም እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው በየቀኑ እየመጣ እስራኤልን እንደሚገዳደር ታያላችሁ? ይህን ሰው ለሚገድል፣ ንጉሡ ብዙ ሀብት ይሰጠዋል፤ ሴት ልጁን ይድርለታል፣ የአባቱንም ቤት በእስራኤል ዘንድ ከግብር ነጻ ያደርገዋል” ይባባሉ ነበር።