1 ሳሙኤል 14:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በብንያም ግዛት በጊብዓ የነበሩ የሳኦል ዘቦች፣ የፍልስጥኤም ሰራዊት በየአቅጣጫው መበታተኑን አዩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በብንያም ግዛት በጊብዓ የነበሩ የሳኦል ጠባቂዎች፥ የፍልስጥኤም ሠራዊት በየአቅጣጫው መበታተኑን አዩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሳኦል ወታደሮች የብንያም ግዛት በሆነችው በጊብዓ መሽገው ሁኔታውን ሁሉ በመጠባበቅ ላይ ሳሉ በመታወክ የሚሸሹትን ፍልስጥኤማውያን አዩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በብንያም ገባዖን ያሉ የሳኦል ዘበኞችም ተመለከቱ፤ እነሆም፥ ሠራዊቱ ወዲህና ወዲያ እየተራወጡ ተበታተኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በብንያም ጊብዓ ያሉ የሳኦል ዘበኞችም ተመለከቱ፥ እነሆም፥ ሠራዊቱ ወዲህና ወዲያ እየተራወጡ ተበታተኑ። |
የሦስት መቶው ቀንደ መለከት ድምፅ እንደ ተሰማም እግዚአብሔር በሰፈሩ ውስጥ ያለው ሰው አንዱ በሌላው ላይ ሰይፉን እንዲመዝበት አደረገ፤ ሰራዊቱ በጽሬራ አቅጣጫ ወደ ቤትሺጣ፣ ከዚያም ዐልፈው በጠባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልምሖላ ድንበር ድረስ ሸሽተው ሄዱ።
በሰፈር በዕርሻ ላይና በሕዝብ ሁሉ መካከል ሽብር ሆነ፤ ከተማ ጠባቂዎችና አደጋ ጣዮችም ሁሉ ተንቀጠቀጡ፤ ምድሪቱም ተናወጠች፤ ሽብሩም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ ነበር።
ሳኦልም ዐብረውት የነበሩትን ሰዎች፣ “እስኪ፣ ሰራዊቱን ቍጠሩና ማን ከዚህ እንደ ሄደ እዩ” አላቸው። ይህን ባደረጉ ጊዜም ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው በዚያ አልነበሩም።
ከዚያም ሳኦልና ሰዎቹ ተሰብስበው ወደ ውጊያው ሄዱ። እነርሱም ፍልስጥኤማውያን በሰይፋቸው እየተጨፋጨፉ በታላቅ ትርምስ ላይ ሆነው አገኟቸው።