1 ሳሙኤል 13:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ አንድ የፍልስጥኤማውያን ጭፍራ ወደ ማክማስ መተላለፊያ ወጥቶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ አንድ የፍልስጥኤማውያን የጦር ምድብ የሚክማስን መተላለፊያ ለመቆጣጠር ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያን የሚክማስን መተላለፊያ የሚቈጣጠር አንድ ቡድን ላኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ጥቂቶች ከፍልስጥኤማውያን ሰፈር ወደ ማኪማስ መተላለፊያ ወጡ። |
ፍልስጥኤማውያን ሦስት ሺሕ ሠረገሎች፣ ስድስት ሺሕ ፈረሰኞች ቍጥሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ሰራዊት ይዘው እስራኤልን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ ወጥተውም ከቤትአዌን በስተምሥራቅ ባለችው በማክማስ ሰፈሩ።
አንድ ቀን የሳኦል ልጅ ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፣ “ና በሌላ በኩል ወዳለው የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር እንሻገር” አለው። ይህን ግን ለአባቱ አልነገረውም ነበር።